Thursday, December 24, 2015

የሚሊኒየሙ ስምምነት በኢኽዋኖችና በሱፍዬች መሐል?

የሚሊኒየሙ ስምምነት በኢኽዋኖችና በሱፍዬች መሐል?
ኢኽዋኖችና ሱፍዬች የሚሊኒየሙ ስምምነት በተባለው መዘጋጃ ቤት ውስጥ ከተስማሙበትና ከተፈራረሙባቸው ነጥቦች ውስጥ ለናሙና የሚከተሉት 2ቱ ይገኙበታል፡፡
5) ‹‹በየመስጂዱ በሚሰጡ ዳእዋዎች ልዩነት የሚያስነሱ ነጥቦች ርዕስ ሆነው እንዳይቀርቡ በጋራ እናደርጋለን፡፡ ኺላፍ ባለባቸው ነጥቦች ዙርያ ጥያቄ ከተነሳም አንዱን ከሌላው በማያበላልጥ መልኩ መልስ እንዲሰጥባቸው ማድረግ እንደሚገባ ተማምነን ይህንኑ በጋራ ተስማምተናል፡፡››
ለዚህ የጥመት ስምምነት ትንሽ መልሶች
- ‹‹በየመስጂዱ በሚሰጡ ዳእዋዎች ልዩነት የሚያስነሱ ነጥቦች ርዕስ ሆነው እንዳይቀርቡ በጋራ እናደርጋለን፡፡›› ብለዋል፡፡
ሃቅና ባጢል እማ በፍፁም አብረው አይሄዱም ልዩነትም ያስነሳሉ፡፡ ለምሳሌ ሽርክ ሲወገዝ ሽርክ ላይ የወደቁና፣ ኹራፋት ተከታዬች ይከፋሉ፡፡ ቢድዐ ሲጋለጥ ቢድዐ አራማጆች ይከፋሉ፣ በእርግጥም በሱንይና በሙብተዲ መሃል ልዩነት ይነሳል፡፡ ታድያ መስጂድ ውስጥ የሚሰጠው ዳዕዋ ልዩነት እንዳያስነሳ በሚል የተውሂድና ሱና ስብከት፣ ሽርክና ቢድዓና ማውገዝ ሊቀር ነውን?
ዳሩ እናውቃቸዋለን ሱፍያም የመጅሊሱን ስልጣን በያዙ ጊዜ የተውሂድ ዳዕዋ እንዳይደረግ ብሎም ወደ ተውሂድ የሚጣሩ ወንድሞችን ሲያስፈራሩ ብሎም ከኢኽዋን ጋር በመመሳጠር ለደህንነት ሲያስይዙም ነበር፡፡
- በተለያያችሁ ጊዜ ወደ ቁርዓንና ሀዲስ ተመለሱ እንጂ አንዱ ከአንዱ እንዳይከፋ በሚል ሃቅን ጥላችሁ ሂዱ የሚል ሀይማኖት ኖሮን አያውቅም፡፡ መሃይማንና አውቆ አጥፊዎች ቢያውቁ ኖሮ
ማስረጃዎች
ሃቅን መከተል ግዴታችን ነው አላህ እንዲህ ይላል
فَلَا وَرَبِّكَ لَا يُؤْمِنُونَ حَتَّىٰ يُحَكِّمُوكَ فِيمَا شَجَرَ بَيْنَهُمْ ثُمَّ لَا يَجِدُوا۟ فِىٓ أَنفُسِهِمْ حَرَجًا مِّمَّا قَضَيْتَ وَيُسَلِّمُوا۟ تَسْلِيمًا
በጌታህም እምላለሁ በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ እስከሚያስፈርዱህ ከዚያም ከፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው ውስጥ ጭንቀትን እስከማያገኙና ፍጹም መታዘዝንም እስከሚታዘዙ ድረስ አያምኑም፤ (ምእመን አይኾኑም)፡፡
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَطِيعُوا۟ ٱللَّهَ وَأَطِيعُوا۟ ٱلرَّسُولَ وَأُو۟لِى ٱلْأَمْرِ مِنكُمْ ۖ فَإِن تَنَٰزَعْتُمْ فِى شَىْءٍ فَرُدُّوهُ إِلَى ٱللَّهِ وَٱلرَّسُولِ إِن كُنتُمْ تُؤْمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْءَاخِرِ ۚ ذَٰلِكَ خَيْرٌ وَأَحْسَنُ تَأْوِيلًا
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ መልክተኛውንና ከእናንተም የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ፡፡ በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትኾኑ (የተከራከራችሁበትን ነገር) ወደ አላህና ወደ መልክተኛው መልሱት፡፡ ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው፡፡
በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትኾኑ (የተከራከራችሁበትን ነገር) ወደ አላህና ወደ መልክተኛው መልሱት እንጂ የተባለው የእኛዎቹ ዲንን አበላሾች እንዳሉት ‹‹አንዱን ከሌላው በማያበላልጥ መልኩ መልስ እንዲሰጥባቸው ማድረግ እንደሚገባ ተማምነን ይህንኑ በጋራ ተስማምተናል›› ብሎ መደስኮርና መፈራረም አልነበረም፡፡
6) ‹‹የነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መውሊድ አከባበር ሥነ-ሥርዐት ብሔራዊ በዓልነቱ ታውቆ ይከበራል፡፡ ስለ በዐሉም ሆነ የነብዩን ሲራ አስመልክቶ የሚሰጡ ትምህርቶች በሁሉም ወገኖች ያለ ተብዲዕ (ቢድዐ ነው ሳንል)፣ ያለ ተፍሲቅ (ፊስቅ ወንጀል አለበት ሳንል)፣ ያለ ተሸሪክና (ሽርክ አለው ሳይባልና)፣ ያለ ተክፊር እንዲከናወኑ ለማድረግ በጋራ እንሰራለን፡፡››
ይህቺ እርኩስ የሆነች ስምምነት ናት፡፡ የሽርክ መናሀርያ የሆነውን መውሊድ ‹‹ያለ ተሸሪክና (ሽርክ አለው ሳይባልና)፣ ቢድዐ ነው ሳንል›› ብሎ መስማማት፣ ከዚህም አልፎ ‹‹ያለ ተፍሲቅ (ፊስቅ የለውም)›› ብሎ ወንድና ሴት ተደባልቀው የሚጨፍሩበትን፣ ይህን አደንዛዥ ቅጠል ጫት የሚቃምበትን፣ ሲጋራ የሚጨስበትን አረ ስንቱ እርኩስ ነገር ያለበትን እንዲከበር መስማማታቸው በጥፋት ላይ የተሰባሰቡ ለመሆናቸው ማስረጃ ነው፡፡
አላህ በምን ጉዳይ እንድንረዳዳ እና በምን ጉዳይ እንዳንረዳዳ እንዲህ ሲል በአንድ አንቀፅ ላይ ያስቀምጥልናል
وَتَعَاوَنُوا۟ عَلَى ٱلْبِرِّ وَٱلتَّقْوَىٰ ۖ وَلَا تَعَاوَنُوا۟ عَلَى ٱلْإِثْمِ وَٱلْعُدْوَٰنِ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ
በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ ግን በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡
ይህ ነው እንግዲህ የቢድዐ ሰዎች ሴራ ዲንን፣ ሱናን፣ ተውሂድን ስሜታቸውን በመከተል መናድ፡፡ ድንገት እኛ እኮ አሳማሪዎች ነን ይሉ ይሆናል፡፡ ታድያ ምነው በሱና ላይ መቆም አቃታቸው?
ምነው ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምና) ሰሃባዎች፣ ሰለፉነ ሷሊሁን የነበሩት መንገድ ላይ ለምን መቆም አቃታቸው?
አላህ እንዲህ ይላል
وَإِذَا قِيلَ لَهُمْ لَا تُفْسِدُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ قَالُوٓا۟ إِنَّمَا نَحْنُ مُصْلِحُونَ
ለነርሱም «በምድር ላይ አታበላሹ» በተባሉ ጊዜ «እኛ አሳማሪዎች ብቻ ነን» ይላሉ፡፡
أَلَآ إِنَّهُمْ هُمُ ٱلْمُفْسِدُونَ وَلَٰكِن لَّا يَشْعُرُونَ
ንቁ እነርሱ አጥፊዎቹ እነሱው ናቸው፤ ግን አያውቁም፡፡
ኢህዋኖች ከሱፍዬም፣ ከቀብር አምላኪውም፣ ከቲጃንዩም፣ ከሺዐውም፣ ከካፊሩም ጋር አንድ ነን ይላሉ መሆንም አያቅታቸውም፡፡ እነሱ ጦርነታቸውና ጠላትነታቸውን የሚያሳዩት ሰለፍዬች፣ የተውሂድ ተጣሪዎች፣ የሱና አፍቃሪዎች ላይ ነው፡፡
ዳሩ አደለም መዘጋጃ ቤት፣ ቤተ መንግስትም ገብተው ቢፈራረሙት ባጢል ሃቅ አይሆንም፡፡
የውሸት ስምምነትና የውሸት አንድነት ሁሌም ውሸት ነው፡፡ ይሀው የውሸቱ አንድነት መዝለቅ አቅቶት አሁን እርስ በእርስ ተከዳዱ፡፡ምስጋና ሁሉ ለአላህ ይተገባ ነው፣ አላህ ዲን አበላሾችን ድባቅ መታቸው፡፡
የስምምነታቸውን ወረቀት ከነፊርማቸው ማረጋገጥ የፈለገ ከሚከተለው ሊንክ ዳውንሎድ ያድርግ፡፡
https://goo.gl/80CXch
የአላህ ሰላትና ሰላም በነብያት መደምደሚያ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸውና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡

Friday, November 27, 2015

የእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች) ትምህርት ከኢርሻድ ኪታብ - ክፍል 7




ለእስልምና ማእዘናት ማስረጃችን

ከቁርአን

አላህ በቁርአን ላይ እንዲህ ብሏል


لَّيْسَ الْبِرَّ أَن تُوَلُّوا وُجُوهَكُمْ قِبَلَ الْمَشْرِقِ وَالْمَغْرِبِ وَلَٰكِنَّ الْبِرَّ مَنْ آمَنَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَالْمَلَائِكَةِ وَالْكِتَابِ وَالنَّبِيِّينَ وَآتَى الْمَالَ عَلَىٰ حُبِّهِ ذَوِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينَ وَابْنَ السَّبِيلِ وَالسَّائِلِينَ وَفِي الرِّقَابِ وَأَقَامَ الصَّلَاةَ وَآتَى الزَّكَاةَ وَالْمُوفُونَ بِعَهْدِهِمْ إِذَا عَاهَدُوا ۖ وَالصَّابِرِينَ فِي الْبَأْسَاءِ وَالضَّرَّاءِ وَحِينَ الْبَأْسِ ۗ أُولَٰئِكَ الَّذِينَ صَدَقُوا ۖ وَأُولَٰئِكَ هُمُ الْمُتَّقُونَ

﴿البقرة: ١٧٧﴾
“መልካም ስራ ፊቶቻችሁን ወደ ምስራቅና ምዕራብ አቅጣጫ ማዞር አይደለም። ግን መልካም ስራ በአላህና በመጨረሻው ቀን፣ በመላክትም፣ በመፀሐፋም፣ በነብያትም፣ ያመነ ... ነው።”
አላህ በቁርአን ላይ እንዲህ ብሏል 
﴿القمر: ٤٩﴾ إِنَّا كُلَّ شَيْءٍ خَلَقْنَاهُ بِقَدَرٍ

“እኛ ሁሉንም ነገር በልክ(ቀደር)ፈጠርነው።”

Tuesday, October 20, 2015

#‎አላህ_ይጠብቃት‬



#‎አላህ_ይጠብቃት‬

በፀዳችው ሀገር በሱዑዲ ሜዳ
በነብዩ ምድር በቅዱሷ ጓዳ
ተውሒድ ተንሰራፍቶ ሽርኩ ሲሽመደመድ
ሱና ምደሩን ሞልቶት ቢድዓ ሲቆራመድ
ያየ በሽተኛ የታወረ ቀልቡ
ከኢብሊስ ጋር ዘምቶ የከረፋ ልቡ
ሌት ተቀን ይተጋል ስም እያጎደፈ
በተውሒድ አገር ላይ ዋሽቶ እየቀጠፈ።
አላህ ይጠብቃት ሱዑዲን ከሴረኛ
ከኢራን ሙሽሪኮች ከኢኽዋን መጋኛ
ከ"ዴሞክራሲ" ዛር ከምዕራብ ቅጥረኛ።
 
 

የውጫጭ ጥርቅም



የውጫጭ ጥርቅም

የዛ ጀግና ብዕር የሸኽ ረቢዕ ምላሽ
የሱፍያን በሽታ በ”ረዶቹ” አስታጋሽ
የኢኽዋንን ቅጥፈት በሱና አፈራራሽ
በቢድዓ አጨብጫቢ ውሸታም ጉሮሮ
የሸኽ ረቢዕ ትችት ውስጡ ተሰንቅሮ 
እንደ ብርቱው እሾህ ገብቶ ተቀርቅሮ
አላስቆም አላስኬድ ብሎት አስቸግሮ
በቁርአን በሓዲስ ቢይዘው ወጥሮ
በርታ ቀጥል አለው የዘመን ዑለማ
ኢብኑ ባዝ አልባኒ ሌላ እሱን የሰማ
ሙቅቢልም ወደደው ፈውዛን አወደሰው
ዑሰይሚን ተው አለ የዘለፈውን ሰው
በኒህ ከዋክብቶች በኡማው ጨረቃ
መልካም ተብሎለት ተሹሞ ሲያበቃ
ውጫጩ ቢንጫጫ ያቅሙን ድንበር ሰብሮ
ኢኽዋኑ ከተክፊር አንድ ላይ አብሮ
ረቢዕ ላይ ቢዘምትም ሓዳዲን ጨምሮ 
ምን ይጎዳል አቦ! የመንደር ጫጫታ
የውጫጭ ጥርቅም የጃሂል እሪታ!


Friday, October 2, 2015

የእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች) ትምህርት ከኢርሻድ ኪታብ - ክፍል 6



ለእስልምና ማእዘናት ማስረጃችን

ከሓዲስ

أنْ تُؤْمِنَ بِاَللَّهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ، وَتُؤْمِنَ بِالْقَدَرِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ.


َرَوَاهُ مُسْلِمٌ

ነብዩ ሙሀመድ(ሰለላ ዐለይሂ ወሰላም)በሶሒሕ ሐዲስ እንዲህ ብለዋል ፦ “ እምነት(ኢማን)ማለት በአላህ ማመን፣ በመፃሀፋት ማመን፣ በመልእክተኞች ማመን፣ በመጨረሻው ቀን ማመን፣ በቀደር(በአላህ ውሳኔ) በጀም ከፋም ማመን ነው።

ሓዲሱን ሙስሊም ዘግቦታል።
 

Saturday, September 5, 2015

የ “ዘመን መለወጫ” ኮተቶች



የ “ዘመን መለወጫ” ኮተቶች


ኢትዮጵያ በምትከተለው ክርስቲያናዊው የዘመን አቆጣጠር መሰረት አዲስ አመት ሊገባ የያዝነው አመት እየተጠናቀቀ ነው፡፡ ታዲያ ይህን ክስተት ተከትሎ የሚፈፀሙ እምነትን የሚጎዱ በርካታ ጥፋቶች አሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ
1. ቀዳሚው ድግምትና ጥንቆላ ነው፡፡ በሃገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ነሀሴ ሊጠናቀቅ ሲል በየጠንቋዩ ቤት የሚልከሰከሱት እጅግ ብዙ ናቸው፡፡ ከዚያም አምስቱ ወይም ስድስቱ የጳጉሜ ቀናት መንገዶች በድግምት ስራዎች ይሞላሉ፡፡ በነዚህ ቀናት ማልዶ የወጣ ሰው እንዲራመዳቸው ታስቦ በጎረቤት መተላለፊያ እና ህዝብ በሚያዘወትራቸው መንገዶች ላይ ፍየሎች፣ ዶሮዎች፣ ድመቶች፣ ጥንቸሎች ወዘተ ታርደው ይጣላሉ፡፡ በደም የተነከሩ ሳንቲሞች፣ ብሮች፣ ጌጣ-ጌጦች፣ የተለያዩ ቁሳቁሶች እዚህም እዚያም ወድቀው ይታያሉ፡፡ ጥንቆላና ድግምት
- ከኢስላም የሚያስወጡ ከባባድ ወንጀሎች ናቸው፡፡
)وَاتَّبَعُوا مَا تَتْلُو الشَّيَاطِينُ عَلَى مُلْكِ سُلَيْمَانَ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَانُ وَلَكِنَّ الشَّيَاطِينَ كَفَرُوا يُعَلِّمُونَ النَّاسَ السِّحْرَ( البقرة: ١٠٢
“በሱለይማን ዘመነ-መንግስት ሸይጧኖች የሚያነቡትንም (ድግምት) ተከተሉ፡፡ ሱለይማን ግን አልካደም (ድግምተኛ አልነበረምና፡፡) ግና ሸይጧኖች ሰዎችን ድግምት የሚያስተምሩ ሲሆኑ ካዱ፡፡” [አልበቀራህ፡ 102] ነብዩም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡- {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ በሚናገረው ያመነ፣ በሙሐመድ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ላይ በወረደው ክዷል፡፡} [አስሶሒሐህ፡ 3387]
- ደጋሚዎችና ከነሱ ዘንድ የሚመላለሱ ሰዎች መቼም ቢሆን ስኬት የላቸውም፡፡ ጌታችን እንዲህ ይላል፡- “ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናውም፡፡” [ጧሃ፡ 69]
- ደጋሚዎች የሰዎችን ገንዘብ በማታለል የሚበዘብዙ መዥገሮች ናቸው፡፡ ገንዘቡን ለነሱ የሚሰጥ አካልም አላህ ፊት ተጠያቂ ነው፡፡ ነብዩ ዐለይሂስሰላም እንዲህ ብለዋል፡- {የኣደም ልጅ በቂያማህ ቀን አምስት ነገሮችን ሳይጠየቅ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም፡፡ እድሜውን በምን እንዳጠፋው፤ ወጣትነቱን በምን እንደጨረሰው፤ ገንዘቡን ከየት እንዳመጣው፤ እንዲሁም በምን እንዳወጣው፤ ባወቀው ምን እንደሰራ፡፡} [አስሶሒሐህ፡ 946]
- ደጋሚዎች የነገር ቋቶች የማህበራዊ ህይወት ጠንቆች ናቸው፡፡ የተቸገረ ደንበኛቸው መፍተሄ ፈልጎ ሲመጣባቸው በብዛት የችግሩ መንስኤ የሆነው ወይ ጎረቤቱ፣ ወይ ዘመዱ ወይ ደግሞ የቤተሰቡ አባል እንደሆነ በመጠቆም ሰዎች ውስጣቸው እንዲሻክር አለመተማመን እንዲነግስ ያደርጋሉ፡፡ በድግምቶቹ ምክንያት የጤና መጓደል፣ የትዳር መፍረስ፣ የዝምድና መቆራረጥ፣ የጎረቤቶች በጎሪጥ መተያየት አልፎም ደም የሚያቃባ ግጭት እንዲከሰት ሁሉ ሰበብ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
- ጠንቋይና ደጋሚ ዘንድ የሚሄድ ሰው የተነገረውን ባያምን እንኳን ከባድ ቅጣት ይከተለዋል፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡- {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ ስለሆነ ነገር የጠየቀው የአርባ ቀን ሶላቱ ተቀባይነት የለውም፡፡} [ሙስሊም፡ 5957]
2. ሌላው በ “ዘመን መለወጫ” አካባቢ የሚፈፀመው ጥፋት በአንዳንድ አካባቢ ያለው ጳጉሜን ተከትሎ ለዱዓህ መሰባሰብ ነው፡፡ እነዚህ አካላት የጳጉሜ ዱዓህ “መቅቡል ነው” (ተቀባይነት ያለው ነው) በማለት ነው ወቅቱን በዱዓእ የሚያሳልፏት፡፡ በጣም የሚገርመው ለዱዓህ የሚጥጠሩት እስልምናን ያውቃሉ ሰዎችን ያስተምራሉ የሚባሉት ሰዎች መሆናቸው ነው፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “አላህ እውቀትን ከባሪያዎቹ መንጠቅን አይነጥቅም፡፡ ይልቁንም ዑለማዎችን በመውሰድ (በመግደል) እውቀትን ይወስዳል፡፡ ከዚያም ዓሊም እስከማይቀር ድረስ፡፡ በዚያኔ ሰዎች መሀይማንን መሪዎች አድርገው ይይዛሉ፡፡ ሲጠየቁም ያለ እውቀት ፈትዋ ይሰጣሉ፡፡ በዚህም ይጠማሉ፣ ያጠማሉም” ማለታቸው ምንኛ የሚደንቅ ሐቅ ነው?!! ዲን ያስተምራሉ ተብለው የሚታሰቡት አካላት ክርስቲያናዊ አቆጣጠርን መሰረት ያደረገ ዒባዳህ እየፈፀሙ ሰዎችን ወደ ጥፋት ሲወስዱ በገሃድ ይታያሉ፡፡
3. ሌላኛው የ “ዘመን መለወጫን” ተከትሎ የሚፈፀመው ጥፋት መስከረም አንድን ወይም እንቁጣጣሽን ማክበር ነው፡፡ አቆጣጠሩ ሀገራዊ እንጂ እምነታዊ መሰረት እንደሌለው ሊያሳምኑ በከንቱ የሚዳክሩ ሰዎች አሉ፡፡ ነገሩ እጅጉን የፈጠጠ እውነታ ሆኖ ሳለ በዚህ ላይ የሚሸወድ መኖሩ እጅጉን የሚደንቅ ነው፡፡ ብቻ ለማንም እንደማይሰወር ባስብም ለማስታወስ ያክል አቆጣጠሩ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው በሚሲዮናውያን መሆኑ፣ አመቱ ሲፃፍ መጨረሻ ላይ “ዓመተ ምህረት” መባሉ፣ የነብዩ ዒሳን (ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) መወለድ መሰረት ያደረገ እንደሆነ መሞገታቸው እንዲሁም ይበልጥ ለማረጋገጥ የ “ዘመን መለወጫ” ወቅት ላይ “እንኳን ከዘመነ ምንትስ ወደ ዘመነ ምንትስ አደረሳችሁ” ማለታቸው ጥሩ ጠቋሚ ናቸው፡፡
ስለዚህ ከየትኛውም ከአይሁድ፣ ከክርስቲያን እና ከሌሎች እምነቶች ጋር ከሚያመሳስሉ ነገሮች እራስን መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “በሰዎች የተመሳሰለ ከነሱው ነው” ይላሉና፡፡
ወሶለላሁ ዐላ ነቢይዪና ሙሐመዲን ወዐላ ኣሊሂ ወሶሕቢሂ ወሰለም፡፡

(ኢብኑ ሙነወር፣ ነሐሴ 26/2007)
 

Wednesday, July 29, 2015

እኚህ ናቸው ሰለፎቼ (5)

 
እኚህ ናቸው ሰለፎቼ (5)


በ ወንድም Ibnu Munewer

ሁለት የቢድዐ ተከታዮች ሙሐመድ ኢብኑ ሲሪን ዘንድ ገቡና
"የበክር አባት ሆይ የሆነ ሐዲሥ እናውራህ?" አሉት።
"አይሆንም " አለ።
"ከአላህ ኪታብ የሆነች አንቀፅ እናንብብልህ?" አሉ።
"አይሆንም። ትወጡልኛላችሁ ያለበለዚያ እኔ እወጣላችኋለሁ" አላቸው።
በቦታው የነበሩ የተወሰኑ ሰዎች "የበክር አባት ሆይ! ምን ነበር ከአላህ ኪታብ (ከቁርኣን) አንቀፅ ቢያነቡልህ ምን ችግር ነበረው?” አሉት፡፡
ይህኔ ሙሐመድ ኢብኑ ሲሪን እንዲህ አለ፡- “እኔ የሆነች የቁርኣን አንቀፅን ቀርተው አዛብተው እንዳያቀርቧት ከዚያም ያ ያዛቡት ነገር ልቤ ላይ እንዳይቀር ሰግቼ ነው” አለ፡፡ [አስሱናህ፣ ዐብዱላህ ኢብኒልኢማም አሕመድ፡ 1/138]
ይህን ከታላቅ ሰው የወጣ ታላቅ ትውፊት በሚገባ ያጢኑት፡፡ በሚገባም ይስሩበት፡፡ የህይወት መመሪያም ያድርጉት፡፡ ጆሮዎትን ለሙብተዲዕ አያመቻቹ፡፡ “ጥሩ ጥሩን እወስዳለሁ፣ መጥፎ መጥፎውን እተዋለሁ” እያሉ አይፈላሰፉ፡፡ ጥሩ እና መጥፎ ከለየህ እድለኛ ነህ ጎሽ! ባይሆን ሙብተዲዕ ከምታዳምጥ ቁጭ ብለህ አስተምር፡፡ አዋ!! ሙሐመድ ኢብኑ ሲሪን ታላቅ ታቢዒይ ነው፣ ሁሉ የሚመሰክርለት ታላቅ ዐሊም፡፡ ግና ከቢድዐ አደጋ በእውቀቱ አልተማመነም፡፡ ታዲያ እኛ የምንተማመነው በምናችን ነው?! ነው ወይስ እውቀታችን ከሙሐመድ ኢብኑ ሲሪን በላይ ነው? ይልቅ እራስህን ጠብቅ፡፡ “ሹቡሃት ሲበዛ ጠላፊዎች ናቸው!! ልቦች ደግሞ ደካሞች ናቸው” ይላሉ፡፡ የቢድዐን አደጋ እና የልብን ደካማነት የሚያውቁት ጠቢባን፡፡ በቢድዐ ቫይረስ የተበከሉ ግብዞች ግን ጆሯቸውን ለሙብተዲዖች ይጥላሉ፤ ከሙብተዲዕ ስር ሊቀሩ ይንበረከካሉ፤ የሙብተዲዖችን ድስኩር ለመስማት መጅሊስ ያጨናንቃሉ፡፡ የሙብተዲዖችን መርዛማ ኪታቦች በገዛ ገንዘባቸው ይገዛሉ፡፡ “ምነው?” ሲባሉ ችግሩን አውቃለሁ፡፡ እየመረጥኩ እወስዳለሁ ብየ ነው” ይላሉ፡፡ ዐጂብ ፍልስፍና!! ዐጂብ የሆነ በራስ መኮፈስ፡፡ ብዙም ሳይቆዩ ዋጋቸውን ያገኛሉ፡፡ ለሱና ያላቸውን ፍቅር፣ ለቢድዐ ያላቸውን ጥላቻ ዐቂደቱልወላእ ወልበራእን በራሳቸው ሳንቲም ከልባቸው ውስጥ ይረሽናሉ፡፡ ከዚያም ይህን ቅጥ ያጣ “ስፋታቸውን” መንቃት፣ አርቆ ማሰብ ያደርጉታል፡፡
ይህን ለመፃፍ ያነሳሳኝ በቅርቡ በታላቁ ሐበሻዊ ዐሊም ሙሐመድ አማን አልጃሚ ረሒመሁላህ ላይ የተቀጠፉ አስቀያሚ ውንጀላዎችን ማየቴ ነው፡፡ ሙሐመድ አማንን የመንግስት ቅጥረኛ እንደነበሩ፣ ዑለማዎችን አሳልፈው ይሰጡ የነበሩ ሰላይ እንደነበሩ፣ ወዘተ በሚያስጠሉ ቃላት ሲወርፉ ማየት ምንኛ የሚያሳዝን ነገር ነው? በርግጥ ከቢድዐ ሰዎች ከዚህ የተሻለ መጠበቅ የዋህነት ነው፡፡ የቢድዐ ሰዎች ዑለማን ስለማክበር የሚደሰኩሩት ካንገት በላይ እንደሆነ ያሳየ ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡ “ዑለማን እናክብር” ሲሉ የሚፈልጉት የቢድዐ ቁንጮዎቻቸውን እንድናንቆለጳጵስ እንጂ የሱና ዑለማዎችንማ ይሄው በሌሉበት በሀሰት እየወነጀሏቸው ነው፡፡ አላማቸው ወጣቱን ከሱና ዑለማ ማራቅ ነው፣ ከዚያም ጭፍን የነሱ ተከታይ ማድረግ፡፡ ዐረብ የሆኑ ኢኽዋኖች ሸይኽ ሙሐመድ አማን አልጃሚን የትኛውንም ሰለፊ ከሚወርፉት በላይ ይወርፏቸዋል፣ አዲስ አንጃ እንደመሰረቱም ይቀጥፉባቸዋል፡፡ ከማንም በላይ እሳቸው ላይ ያነጣጠሩት ዐረብ ስላልሆኑ ነው፡፡ ሸይኽ አልጃሚ ምንም እንኳን በታላላቅ የሱና ዑለማዎች እጅግ የሚገርም አድናቆትን ቢቸሩም ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ስማቸውንም የሚያውቀው ጥቂት ነው፡፡ ስንቱ የሱፍያ ሸይኾች ድንበር ባለፈ መልኩ በሚሞካሹበት ምድር የሳቸው ግን ታሪካቸውም አይወራም፡፡ ምክንያቱ ግልፅ ነው፡፡ ሸይኹ ሲበዛ ሱናህ ላይ ብርቱ ነበሩ ረሒመሁላህ፡፡ ሸይኹ የታላላቅ የሱና ዑለማዎች ሸይኽ ናቸው፡፡ ተማሪዎቻቸው እንኳን በአለም አቀፍ ደረጃ የሚያበሩ ደማቅ ከዋክብት ናቸው፡፡
እዚህ ግባ የማይባሉ የሰፈር ሸይኾችን ሳይቀር “ከነ ሸይኽ ፈውዛን በምን ያንሳሉ? ሃበሻ ስለሆኑ ነው እንዴ?” እያሉ ስውር በሆነ መልኩ ሌሎች የሱና ዑለማዎችን በዘረኝነት እየወረፉ የቢድዐ ድሪቶዎቻቸውን ለመቆለል የሚጣጣሩ ሰዎች ይሄን “ለወንዝ ሰው” መቆርቆራቸውን ግን ለሸይኽ ሙሐመድ አማን አልጃሚ ሲሆን አይተገብሩትም፡፡
የቢድዐ አጫፋሪዎች በጭፍን የሳዑዲ ዑለማዎችን እንደምንከተል ያስተጋባሉ፡፡ ይሄ አይን ያወጣ ቅጥፈት ነው፡፡ መለኪያችን አካሄዳቸው እንጂ ዜግነታቸው አይደለም፡፡ አዎ እንደነሱ “የሀገር ውስጥ” እና “የባህር ማዶ” በሚል ዑለማዎችን ለሁለት አንከፍልም፡፡ አዎ ታላላቅ የሱና ዑለማዎችን “የሀገራችን” አይደሉም በሚል ትምህርቶቻቸውን ገሸሽ አናደርግም፡፡ ይሄ የቦዘኔ እስፖርተኞች አካሄድ እንጂ የዲን አካሄድ አይደለምና፡፡ ይሄኮ በጭፍን ቲፎዞ የሚኮንበት ኳስ ወይም ሩጫ አይደለም፡፡ ስለዚህ የውጭም ቢሆኑ ሱኒዎችን እንወዳለን፡፡ የውስጥም ቢሆኑ ሙብተዲዖችን እንጠላለን፡፡ እነ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ፣ ኢብኑ ዑሠይሚን፣ ፈውዛን፣ ረቢዕ፣ አልሉሐይዳን፣ አልዐባድ፣ ዑበይድ፣… የወደድናቸው ሳኡዲያውያን ስለሆኑ ሳይሆን ጠንካራ የሱና ሰዎች ስለሆኑ ነው፡፡ እንጂማ እነ ሰልማን አልዐወዳህ፣ ሰፈር ሐዋሊ፣ ዓይዱልቀርኒ፣ ዐሪፊን እና መሰሎቻቸውን ሳዑዲያውያን መሆናቸው እንድንወዳቸው አያደርገንም፡፡ የቢድዐ አካሄዳቸው እንድንጠላቸው ያስገድደናልና፡፡ እነ ሐሰን አልበና፣ ሰይድ ቁጥብ፣ ቀርዷዊ፣ … ወዘተ የምንጠላቸው የቢድዐ ቁንጮዎች ስለሆኑ እንጂ ግብፃውያን ስለሆኑ አይደለም፡፡ በጭራሽ!! እንጂማ እዚያው ግብፅ ውስጥ እነ ሙሐመድ ሰዒድ ረስላንን፣ እነ ሐሰን ዐብዱልወሃብ አልበናን፣ እነ ጦልዐት ዘህራንን፣... እንወዳለን፡፡ ከሌላውም አለም እነ አልባኒን፣ ሙቅቢልን፣ ሙሐመድ አሚን አሽሺንቂጢን፣ እነ ዑመር ፈላታን፣ እነ ሙሐመድ ዐብዱልወሃብ አልወሷቢን፣ እነ ሙሐመድ ዐሊ ፈርኩስን፣ … የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ቢሆኑም እንወዳለን፡፡ የወደድናቸው የውጭ የማድነቅ አባዜ ኖሮብን ሳይሆን የተከተሉት መንገድ አንድነት ነው፡፡ የሀገሬን አልጠላም፡፡ ለምንስ ሲባል እጠላለሁ?! እሄው የሀረሩን ጀግና ሸይኽ ሙሐመድ አማን አልጃሚን እና መሰሎቻቸውን እጅግ በጣም እወዳቸዋለሁ፡፡ የወደድኳቸው ግን ኢትዮጵያዊ ስለሆኑ አይደለም፣ ብርቱ የሱናህ ሰው ስለነበሩ እንጂ፣ ረሒመሁላህ፡፡ መስመራቸውን የቢድዐ መስመር ያደረጉትን በሙሉ ዜግነታቸውን ከግምት ሳላስገባ አልወዳቸውም፡፡
እዚጋ “ሁሉስ ሙስሊሞች አይደሉ? ምንድን ነው እየመረጡ መውደድ?” የሚል ይኖር ይሆናል፣ ጊዜው ዐጃዒብ የበዛበት ነውና፡፡ በዚህ ረገድ የተነገሩ ጥቂት የቀደምቶቻችንን ትውፊቶች በመጥቀስ ፅሁፌን ልዝጋ
1. “እኔ ከአህሉ ሱንናህ የሆነ ሰው መሞቱ ሲነገረኝ ልክ ከአካል ክፍሎቼ የተወሰነውን ያጣው ያክል እሆናለሁ!!” አዩብ አስሰኽቲያኒ ረሒመሁላህ፡፡
2. “በምስራቅ ስለሚገኝ አንድ የሱና ሰው፣ እንዲሁም በምእራብ ስለሚገኝ ሌላ የሱና ሰው ከሰማህ ሰላምታ ላክላቸው፡፡ ዱዐም አድርግላቸው፡፡ የሱና እና የጀማዓ ሰዎች ምንኛ ጥቂቶች ናቸው?!!” ሱፍያን አሥሠውሪ ረሒመሁላህ፡፡
3. አሰድ ኢብኑ ሙሳ እንዲህ ይላል፡- “ሱፍያን ኢብኑ ዑየይናህ ዘንድ ነበርን፡፡ የደራወርዲ መርዶ ደረሰው፡፡ (በስህተት ነው እንጂ ሰውየው አልሞተም ነበር፡፡) እጅግ አዘነ፡፡ ቁጭቱንም ግልፅ አወጣው፡፡ ‘ይህን ያክል የምትደርስ አይመስለንም ነበር’ አልነው፡፡ ‘ከአህሉ ሱናህ እኮ ነው!!’” አለ፡፡
4. “ከነችግራቸው የሱናህ ሰዎችን ውደዱ፡፡ እኛንም እናንተንም አላህ በሱናህ እና በጀማዐህ ላይ ይግደለን፡፡” አልኢማም አሕመድ ረሒመሁላህ፡፡
ማሳሰቢያ!
የቢድዐ ሰዎችን እንጠላለን ማለት በጥፋታቸው ልክ እንጂ ከሃዲዎችን የምንጠላውን ያክል ነው ማለት አይደለም፡፡ ወሰላም፡፡

(ኢብኑ ሙነወር፡ ግንቦት 01/2007)

በ ወንድም Ibnu Munewer

Thursday, June 4, 2015

የእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች) ትምህርት ከኢርሻድ ኪታብ; ክፍል 5





የእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች) ትምህርት ከኢርሻድ ኪታብ

ክፍል 5

የእስልምና መሰረታዊ እምነቶች 6 ናቸው

እነሱም፦
1.በአላህ ማመን
2.በመላኢኮች ማመን
3.በመፅሀፍት ማመን
4.በመልክተኞች ማመን
5.በመጨረሻው ቀን ማመን
6.በቀደር (በአላህ ውሳኔ) ማመን 

Saturday, May 9, 2015

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን ‹‹አጫጭሱላቸው››፣ በሽርክ አይሳቅም፡፡








ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን
‹‹አጫጭሱላቸው››፣ በሽርክ አይሳቅም፡፡ 
በአላህ ፈቃድ ወደ መደበኛ ትምህርታችን እንመለሳለን፡፡ ሽርክ አላህ ታላቅ በደል ብሎ የጠራው ነው፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምም) ታላላቅ አጥፊ ወንጀሎችን ሲጠቅሱ ከሽርክ ነው የጀመሩት፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መዲና ተቀምጠው የመን ውስጥ የምትመለከዋ ቀብር እረፍት ነሳችኝ ብለው ነበር፡፡ ዛሬ አላህ ካዘነላቸው ውጭ፣ የሽርክ ጉዳይ ብዙም ቦታ አይሰጠውም ዱዓት በሚባሉት ዘንድ፡፡ አላህ ሁሉንም ተጣሪዎች ነብያቱን አስታጥቆ ወደላከበት አርስት ተውሂድ ይመልሳቸው፡፡ 
በሶዎች ሞባይል ውስጥ በተለይ በጫት ቃሚዎች መሃል አንድ በ ብሉ ቱዝ የሚቀባበሏት አፉ ላይ ጫት የያዘ ወጣት የሚያንጎራጉራት የሽርክ ስንኞች፣ አደብ ማጣት እና ኹራፋት ውስጥ የሚከተሉት ይገኛሉ
1) ‹‹የቦረናው ጌታ ነው እንደ ጡላጊ፣
ትልቁን ጠቃሚ፣
ትንሹን አሳዳጊ››
ይሄ ስንኝ በግልፅ የአላህን መብት አሳልፎ ለቦረናው ሸይኽ እየሰጠ ነው፡፡ ጠቃሚ ጎጂ፣ ሰጪ ነሺ አላህ ብቻ ነው፡፡ አላህ ብቻ ሊያደርገው በሚችለው ጉዳይ ፍጡራንን መጥራት ሽርክ እና ኩፍር ነው፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ደግሞ ከአላህ ውጭ ያለን እየጠራ የሞተ እሳት ገባ ብለዋል፡፡ ነፍሳችንን፣ ቤተሰቦቻችንን ከእሳት በአላህ ፈቃድ በታደግ ግድ ይለናል፡፡ ተውሂድን መማር እና ማስተማር ከምንም በፊት የሚቀደም ፈርድ ነው፡፡
2) ‹‹ፍየል ቅጠል በልታ ትወልዳለች መንታ፣
መቼም እርባን የለው በጫት የተመታ››
እዚህ ጋር በጫት ሱስ የተለከፈ እርባና የለውም ሊል ከሆነ የፈለገው ትክክል ነው፡፡ ከዛ ውጭ ግን ይህን አደንዛዥ ቅጠል ለተቃወሙ እና አልቅምም ላሉ ከሆነ ዉድቅ አባባል ነው፡፡ ወይንም ጫት ቅመን በቀልባችን ነደፍናቸው እያሉ የሚያሰሙት ተረተረት እና እርባና ቢስ ወሬ ውድቅ ነው፡፡ እርባና የሌለው ጫት እየቃመ የአላህን፣ የሚስቱን፣ የልጆቹን፣ የቤተሰቦቹን እና የፍጡራንን መብት ጀዝቦ የማያሟላው ነው፡፡
3) ‹‹ቶሎ በል ቶሎ በል፤
አንድዬ ቶሎ በል፣
እንደ ዘመኑ ሰው ነገ ዛሬ አትበል››
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን ተመልከቱ የዚህ የጫት ቃሚ ድፍረት እና መሃይምነት፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ ‹‹ማንም ሙስሊም በወንጀል እና ዝምድናን በመቁረጥ ዱዓ እስካላደረገ ድረስ አላህ ከሶስት አንዱን ይሰጠዋል፡፡ ወይ የለመነው ይደርሰዋል፣ ወይ ለአኸይራ ያዘገይለታል፣ ወይም አምሳያውን በላ ያነሳለታል››፡፡ አሁንም ነብዩ (አለይሂ ሰላቱ ወሰላም) በዱዓ እንዳንቻኮል ነገረውናል፡፡ አላህን እንዲህ አድርጎ መወሰፍ ምን የሚሉት በሽታ ነው፡፡ አላህ አደብ እና እውቀት ይስጠን፡፡ 
4) ‹‹ዝናቡ ዘነበ ጫቱ ለመለመ፣
የሚቅመው ቢያገኝ እያጉረመረመ››
ኡመተል ኢስላምን ያሽመደመደው፣ ያጀዘበው፣ የአላህንም የፍጡራንንም ሀቅ እንዲያጓድል ሰበብ የሆነው ይህን አደንዛዥ ቅጠል እንዲህ እያሉ ያስተዋውቁታል፡፡ አላህ ወንድም እና እህቶቻንን ከዚህ ሱስ ያውጣልን፡፡
5) ‹‹ወንድነት አይጠቅም ሴትነት አይጎዳ፣
መገኘት ነው እንጂ ከሳዳቶች ጓዳ››
ሳዳቶች ምርጦች ብለው የሚያስባቸው ሰዎች እነዚህ አይነት ሰዎች ዘንድ መጋረጃ ጋርደው የሚጠነቁሉ፣ ጀመዓ ሰላት የማይሰግዱትን ነው፡፡ ሸሪዓችን ከጥሩ ሰዎች ጋር እንድንጎዳኝ ነገሮናል፡፡ ይህ ማለት ግን መጋረጃ ጋርዶ ጫት የሚያኝኩ፣ ለጂን የሚያርዱ ሰዎች ጓዳ እንድንኳትን አይደለም፡፡
አማኝ ሆን አላህን መታዘዝ የእውነተኛ ወልዬች ባህሪ ነው፡፡ ወንዶች መስጂድ ይገኛሉ፣ ቂርዓት ይቀራሉ፣ ዝምድና ይቀጥላሉ በጠቅላላ ወንድም ሴትም አማኞች አላህ እና መልክተኛው ያዘዙትን ይሰራሉ እንጂ ጠንቋይ ቤት ወይንም የጠንቋይ ጓዳ አይመላለሱም፡፡
6) ‹‹አጫጭሱላቸው በሁለቱ ገሌ (ማጨሻ)፣
አንዱም የአብዶዬ ነው፣
አንዱም የኸድር››
ከላይ አብዶዬ የሚሏቸው አብድልቃድር ጀይላኔ (ረሂመሁላህ) ነው፡፡ ኸድር ደግሞ ነብየላህ ኸድርን (አለይ ሰላም) ነው፡፡ ልብ በሉ ብዙ እናቶች እና አባቶች ቡና ይፈላ ይባል እና ቁርስ ጀባ ቃሃ ጀባ እየተባለ እጣን ይጨሳል፡፡ እጣኑም ሲጨስ እንዲህ ከአላህ ውጭ ያሉን የሚጠሩበት ሁኔታ አለ፡፡ አንድ ሰው ቤቱ ላይ ቤቱ ጥሩ ሽታ እንዲኖረው ማጨስ ይችላል፡፡ ይህን የሚያጨሰውን ጭስ ግን ከአምለኮ ጋር አገናኝቶ ለአብድል ቃድር ጀይላኔ እና ለሰይድና ኸድር ሁለት ማጨሻ ተደርጎ አጭሱላቸው ማለት ሽርክ ነው፡፡ 
ስግደቴም፣ እርዴም ወይንም ሀጄም፣ ህይወቴም፣ ሞቴም ለአለማቱ ጌታ ለአላህ ነው፣ አጋር የለውም፡፡ ይህ ነው የኢስላም መልክት፡፡ የሚያሳዝነው ግን ሰዎች ይህን መሰል የሽርክ ስንኞች እና ተግባሮች ለሰዎች ሲያስተላልፉ እየሳቁ፣ ስማው እማ እያሉ ሙድ እየያዙ፣ ብሎ እስቲ ትንሽ ፈታ በል እያሉ ኩፍርን፣ ሽርክን፣ ኹራፋትን ሲቀባበሉ እና ሲስቁ ታያለህ፡፡
እውነት ሽርክ የሚያስቅ ወይንስ እረፍት የሚነሳ አስደንጋጭ ጉዳይ ነው?
አንዳንዶች ባክህ አታካብድ ይላሉ፡፡ ግን ያልገባኝ ሽርክ ያልተካበደ ምን ይሆን ሌላ የሚካበደው አጀንዳ? 
የአላህ ባርያዎች ሆይ! እያንዳንዳችን በተለይ አገራችን ላይ አይን አፍጥጦ ሽርኩ በአደባባይ ላይ፣ በተለያዩ ሚድያዎች ላይ እየተሰራጨ ያለውን አደጋውን ተረድተን፣ ተውሂድን ተምረን ልናስተምር ግድ ይለናል፡፡ ይህም እኛ ላይ የተጣለ አማና ነው፡፡
አላህ ሆይ! አግዘን፣ እውቀትን ጨምርልን፣ ከሽርክ እኛንም ዝርያዎቻችንንም ጠብቀን፡፡ የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት መደምደሚያ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረቦቻቸው እና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡

Thursday, April 2, 2015

የእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች) ትምህርት ከኢርሻድ ኪታብ።  4





ዐቂዳ (የእስልምና መሰረታዊ እምነቶች)

የእስልምና ዓቂዳ ማለት ምን ማለት ነው?

የእስልምና ዓቂዳ ማለት የእስልምና ሃይማኖት መሰረት የሆኑ እምነቶችን እና ተግባሮችን ጠቅሎ የያዘ ነው። የእስልምና ዓቂዳ እስልምናን ከሌሎች ሃይማኖቶች በዋነኝነት የሚለየው ነው። አንድ ሰው ባለው ዓቂዳ መሰረት ሙስሊም(የእስልምናን ዓቂዳ ከያዘ) ወይንም ከሃዲ(የከሃድያንን ዓቂዳ ከያዘ) ይሆናል ።

የእስልምና ህግጋት ባጠቃላይ ሲታዩ ሁለት ናቸው
=> እምነቶች 
 => ስራዎች

ትክክለኛ የእስልምና መሰረታዊ እምነቶች ከዲኑ ዋናውን ክፋል የሚይዙ ናቸው። 
 

Sunday, March 15, 2015

ለእህቴ!





ለእህቴ! 
አሙ ከብሸህ የተባለች ሶሐብያህ ረዲየላሁ ዐንሃ ነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሙስሊሞች ሰራዊት ጋር ለመውጣት ጠይቃ ይከለክሏታል፡፡ ይህኔ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! እኔ እኮ መዋጋት አስቤ አይደለም፡፡ የምፈልገው ቁስለኞቹን ማከም፣ በሽተኞቹን መንከባከብ ነው” አለቻቸው፡፡ 
እሳቸውም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም፡- 
" لولا أن تكون سنة، يقال: خرجت فلانة! لأذنت لك ولكن اجلسي في بيتك "
“እከሌ ወጣች እየተባለ ምሳሌ ተደርጎ እንዳይያዝ ባልሰጋ ኖሮ እፈቅድልሽ ነበር፡፡ ነገር ግን ከቤትሽ ተቀመጪ!!!” አሏት፡፡ 
(አስሶሒሐህ፡ 2740)
እርግጠኛ ነኝ ሊጠቀሙብሽ የሚፈልጉት የሰልፍ አርበኞች ይህን ሐዲሥ ብዙ ይጠመዝዙታል፡፡ ጠብቂ፡፡ አጥጋቢ መልስ መያዝሽን ግን በሚገባ አስቢበት፡፡ ነገ መርማሪው ውስጠ-አዋቂው አላህ ነው፡፡ እራስሽን አታዋርጂ፡፡ መልእክተኛው ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም 
" لا ينبغي لمؤمن أن يذل نفسه، قالوا: وكيف يذل نفسه؟ قال: يتعرض من
البلاء ما لا يطيق "
“ሙእሚን እራሱን ሊያዋርድ አይገባውም” ማለታቸው ላንቺም ነው፡፡ “እንዴት እራሱን ያዋርዳል” ተብለው ሲጠየቁ “ለማይቋቋመው ፈተና እራሱን ማጋፈጡ ነው” ብለዋል፡፡ (አሰሒሐህ፡ 613) 
ያንቺ መውጣትም እራስሽን ከማዋረድሽ ባለፈ ጠብ የሚያደርገው ነገር የለም፡፡ “ብልጥ ማለት በሌላው ላይ ከሚደርሰው የሚማር ነው” ይባላል፡፡ እስካሁን ከደረሰብን መማር ካልቻልን ከስረናል ማለት ነው፡፡
ለሰልፍ ቀስቃሾች!!!
በሚደርሰው ሁሉ ከአላህ ፊት እንዳትጠየቁ ከወዲሁ በንፁህ ህሊና፣ በተረጋጋ መንፈስ አስቡበት፡፡ የሰው ህይወት ቢጠፋ፣ አካል ቢጎድል፣ መሳጂድ በከሃዲዎች ቢረከሱ፣ እህቶቻችን ላይ አሳፋሪና ክብርን የሚነኩ ነገሮች ቢፈፀሙ፣ ሌሎችም ኢስላምንም ሙስሊሞችንም የሚጎዳ ወይም የሚያጎድፍ ነገር ቢፈፀም ፈፃሚው ብቻ ሳይሆን የናንተም እጅ እንዳለበት እንዳትዘነጉ፡፡ ይህንን ነብያዊ ሐዲሥ በጥንቃቄ አስተውሉ፡፡ የመልእክተኛውን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ትእዛዝ ሳያከብሩ ለዲን መቆርቆር የለም፡፡ ጃቢር ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላል፡- “በአንድ ወቅት መንገድ ወጣንና አንዱን ሰው ድንጋይ እራሱን ፈነከተው፡፡ ከዚያም ጁኑብ ሆነና ጓደኞቹን “ተየሙም ማድረግ የምችልበት ፍቃድ” ታገኙልኛላችሁ” ሲል ጠየቀ፡፡ “አይ ውሃ መጠቀም እየቻልክ (ለተየሙም) ፈቃድ አናገኝልህም” አሉት፡፡ በውሃ ታጠበና (ቁስሉ አገርሽቶበት) ሞተ፡፡ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ በመጣን ጊዜ ጉዳዩ ሲነገራቸው፡-
قتلوه قتلهم الله ألا سألوا إذا لم يعلموا فإنما شفاء العي السؤال؟ 
#ገደሉት_አላህ ይግደላቸውና! ካላወቁ አይጠይቁም ነበር? የአለማወቅ መድሃኒቱ መጠየቅ ነው?!” አሉ፡፡ አልባኒ “ሰሒሕ” ብለውታል፡፡ አስተውሉ የተሳሳተ ፈትዋ ሰጥተውት ስለሞተ ነው “ #ገደሉት_አላህ ይግደላቸውና” ያሏቸው፡፡ ዛሬ ግን ሞት፣ ጥፋት፣ ውርደት ወዳለበት ቦታ ነው ሰዎች እየተቀሰቀሱ ያሉት፡፡ 
ወንድሜ ሆይ እህቴ ሆይ! ምንስ ቢደርስብን እንዴት እንዲህ ይባላል ለዲን አይደል የምንወጣው ጂሃድስ ላይ ስንት ነገር ይደርስ የለ” እንደሚባል እጠብቃለሁ፡፡ ክርክር ማስረዘም አልፈልግም፡፡ ከተቀበልክ ታላላቅ የሱና ዑለማዎች ሰልፍ እንደማይፈቀድ አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ በዚህ ላይ የተለየ አቋም ያንፀባረቁት ያለጥርጥር ስሜት የሚጋልባቸው የቢድዐ ጭፍራዎች ብቻ ናቸው፡፡ ደግሞም አስተውል! ጂሃድን ምሳሌ እያደረግክ ጥፋትህን አትጨምር፡፡ በጂሃድ ውስጥ አነሰም በዛም የማሸነፍ እድል አለ፡፡ ለዚያም ነው አልፎ አልፎም ቢሸነፉ ሙስሊሞች ጠላቶቻቸውን ድባቅ እየመቱ የመጡት፡፡ በሰልፍ ውስጥ ግን ማሸነፍ የሚባል ሽታውም የለም፡፡ ያለጥርጥር የምትቃወመው አካል ካላዘነልህ በስተቀር የሚከተለው አደጋ ነው፡፡ ደግሞም ያለነው አፍሪካ መሆኑ አይረሳ፡፡ የህዝብ ጩኸት የቁራ ጩኸት የሆነበት ምድር፡፡ የመብት ጥያቄ በጥይት አረር ምናልባት ከቀለለ በወጠምሾች ዱላ የሚመለስበት ምድር፡፡ እናም እናስተውል፡፡ እስካሁን የደረሰው ይብቃን፡፡ በቁንፅል አስተሳሰብ ላይ ተመርኩዘን፣ በስሜት እየጠየቅን፣ በስሜት እየመለስን፣ በስሜት እየፈረድን እራሳችንን ወገናችንንም ለከፋ አደጋ ባናጋልጥ ጥሩ ነው፡፡ “ዝም ብለን እንመልከት ወይ” አትበለኝ፡፡ ለምን ወደ ከፋው እንሄዳለን ነው ያልኩት፡፡ ዲናችንንም ወገናችንንም የማንም መጫወቻ አናድርገው:: ረጋ ብለን ይህን የሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ ንግግር እንመልከት፡፡ 
وَالْعَجَبُ مِنْ قَوْمٍ أَرَادُوا بِزَعْمِهِمْ نَصْرَ الشَّرْعِ بِعُقُولِهِمْ النَّاقِصَةِ وَأَقْيِسَتِهِمْ الْفَاسِدَةِ . فَكَانَ مَا فَعَلُوهُ مِمَّا جَرَّأَ الْمُلْحِدِينَ أَعْدَاءَ الدِّينِ عَلَيْهِ فَلَا الْإِسْلَامَ نَصَرُوا وَلَا الْأَعْدَاءَ كَسَرُوا
ጌታዬ ሆይ! እኔንም ወገኖቼንም ከክፉ ሁሉ ጠብቀን፣ እውነቱንም አሳየን፡፡ በዲናችንም አትፈትነን፡፡ በየትኛውም ቦታ በዲናችንን የሚፈትኑንንም አካላት አንተው ብቃን፡፡ ላንተ የሚሳንህ የለምና፡፡ 

وصلى الله على نبينا محمد وعلى آله وصحبه وسلم

በ ወንድም Ibnu Munewer 

Thursday, February 26, 2015

የእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች) ትምህርት ከኢርሻድ ኪታብ። 3



የእስልምናን ዓቂዳ ለራሳችን ከተማርን እና ካወቅን ቡሃላ ተግባራዊ ማድረግ አለብን። ተግባራዊ ያልሆነ ማወቅ እወቀት አይባልም። ቀጥሎ የሚመጣው ደረጃ ደግሞ ሰዎችን ወደዚህ ንጹህ እምነት መጥራት ነው። ለራሳችን አውቀናል ወይንም ሰርተናል ብሎ ሰው እየጠመመና እየተሳሳተ ዝም ብሎ ማየት በእስልምና የተወገዘ ተግባር ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን የዚህ እውቀትና ተግባር ባለቤት የሆነውም ዝም በማለቱ እሱ ራሱ ሊጠምም ይችላል።

1. ስለዚህ ባጠቃላይ የእስልምናን ዓቂዳ(የእስልምናን መሰረት)
2. መማር(ማወቅ)፥
3. ተግባራዊ ማድረግ፥
4. ሰዎችን ማስተማር(ጥሪ ማድረግ)፥



እነዚህን 3ት ነገሮችን ስንሰራ ለሚደርስብን ችግር ትዕግስት ማድረግ፥ ግዴታ ነው።

Sunday, February 8, 2015

ከነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ውጭ ሙሉ ንግግሩን የምንቀበልለትም ይሁን መሪ ተደርጎ፤ ሚዛን ሊደረግ የሚገባው አንድም ሰው የለም፡፡



ከነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ውጭ ሙሉ ንግግሩን የምንቀበልለትም ይሁን መሪ ተደርጎ፤ ሚዛን ሊደረግ የሚገባው አንድም ሰው የለም፡፡
=============================
ሸይኽ በክር ኢብን አብደላህ አቡ ዘይድ ‹‹ሁክሙል ኢንቲማ ኢላ ፊርቃ ወል አህዛብ ወል ጀመዓት አል ኢስላሚያ›› በተሰኘው ኪታባቸው ላይ ገፅ 96-97
‹‹ለኡማው አንድን ግለሰብ እንደ መሪ ተደርጎ ሊቀመጥ እና ሰዎች ወደ እርሱ መንገድ ሊጠሩ፤ ወዳጅነትም ጠላትነትም (ለዛ ሰው) ለእርሱ ሲባል ሊፈፀም አይገባም፤ ለእኛ ነብይ እና ለአላህ መልክተኛ ሙሃመድ (ﷺ) ሲቀር፡፡ ከአላህ መልክተኛ ውጭ ያለን በዚህ መንገድ ያስቀመጠ ሰው መንገድ የሳት እና ሙብተዲ (ቢድዓ አራማጅ) ነው፡፡››
ሸይኽል ኢስላም ኢብን ተይሚያ (አላህ ይዘንለት) ‹‹መጅሙኡል ፈትዋ (20/164)›› ላይ እንዲህ ይላል ‹‹አንድን ሰው ለኡማው መርጦ፤ ወደ እርሱ መንገድ መጥራት ሰዎችን በእርሱ ወዳጅ እና ጠላት ማድረግ አይገባም፤ ነብዩን (ﷺ) ሲቀር፡፡
አንድን ንግግርም አስቀምጦ፤ በዛ ንግግር ወዳጅ እና ጠላትን ማድረግ አይቻልም፤ ከነብዩ (ﷺ) ንግግር ውጭ እና ኡማው ኢጅማእ ካደረገበት ውጭ፡፡
ይህ የቢድዐ ሰዎች ተግባር ነው፤ አንድን ሰው እና ለራሳቸው ንግግርን አስቀምጠው፤ ኡማውን የሚበታትኑበት፡፡ ሰውንም በዚህ (እነሱ ባስቀመጡት) ንግግር (ይቀበላል ወይንስ አይቀበልም ብለው)ወዳጅነትን እና ጠላትነትን ያፈርዳሉ››፡፡
ትንሽ ማብራሪያ
=============
አላህ ተከተሉት፤ ታዘዙት፤ አርአያችሁ ነው፤ ተምሳሌታችሁ ነው፤ እኔን መውደዳችሁ ማረጋገጫው እሱን መከተላችሁ ነው፤ ያለው ነብዩ (ﷺ) ብቻ ነው፡፡
ይህ ሆኖ ሳለ፤ ዛሬ ዛሬ ገና አላህ ዘንድ ምን ይሁን ደረጃቸው የማይታወቅ ሰዎች ለኡማው መሪ ተደርገው ተይዘው ‹‹እገሌን ትቀበላለህ ወይንስ አትቀበልም››፤ ‹‹ይህን ተግባር ትቀበላለህ ወይንስ አትቀበልም››፤ ‹‹እነ እገሌ ያሉትን በል፤ ያልተቀበሉትን አትቀበል፤ የተቀበሉትን ተቀበል፤ ዝም ሲሉ ዝም በል፤ ሲናገሩ ተናገር ›› እየተባለ የጥመት እና የቢድዐ አካሄድ አለማችን ላይ በመሰራጨት ይገኛል፡፡ ሌላው የጥመት አባባል ‹‹እገሌ ከእነ ኡስታዝ እንትና ጋር አብሮ አይሰራም›› የሚባል የቡድንተኝነት ወይንም የሂዝብያ መንገድ የሰለፎች መንገድ አይደለም፡፡ ታድያ ከእኛ የሚጠበቀው አንዱን የነብያት ሁሉ ኢማም የሆኑትን ነብይ ቃል መከተል ብቻ ነው፡፡ ሰዎችንም ወዳጅ እና ጠላት ብለን ለመፈረጅ የነብዩን ቃል ይቀበላሉ ወይንስ አይቀበሉም እንጂ ማለት ያለብን፤ ‹‹እገሌን›› ካልተቀበልክ የሚለውን የተሳሳተ አካሄድ እንራቀው፡፡ ሃቅን ከፈለግን፡፡ 
የአላህ መልክተኛን (ﷺ) ብቻ እንጂ መሪ ማድረግ የሚቻለው፤ ሰዎችን መውደድም ሆነ መጥላት የሚቻለው፤ የነብዩን ንግግር ይቀበላል ወይንስ አይቀበልም ተብሎ እንጂ የሌላ ከእርሳቸው ውጭ ያለን ሰው ማንም ይሁን ማን እንዲህ አድርጎ ደረጃ መስጠት አይቻልም፡፡




Sadat Kemal Abu Nuh የተወሰደ።

Friday, January 23, 2015

የእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች) ትምህርት ከኢርሻድ ኪታብ። 2



የእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች) ትምህርት ከኢርሻድ ኪታብ። 

አሰላዋቱ ወሰላሙ ዓላ ረሱሊላሂ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
= የእስልምናን ዓቂዳ መማር በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።
= የ እስልምናን ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች) ማወቅ ማለት የሚከተሉትን ነጥቦች አካቶ የያዘ ነው።
uየእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች) ማለት ምን ማለት ነው?
uየእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች) ማእዘናት የትኞቹ ናቸው?
= የእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች)ን የሚያፈርሱት(ተቃራኒዎች) ተግባራት እና እምነቶች የትኞቹ ናቸው?


የእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች)ን ጎዶሎ የሚያደርጉት ተግባራት እና እምነቶች የትኞቹ ናቸው?

Saturday, January 10, 2015

የእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች) ትምህርት ከኢርሻድ ኪታብ።


بسم الله الرحمن الرحيم


በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።
 
ዝግጅት ፦
በዓብዱልሰመድ መሓመድኑር አሕመድ
 
    الحمد لله رب العالمين،
وصلى الله وسلم على رسوله(صلى الله عليه و سلم)
 
የእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች) ትምህርት ከኢርሻድ ኪታብ