Saturday, June 28, 2014

ተከታታይ የእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች) ትምህርት ከኢርሻድ ኪታብ። ክፍል 5



بسم الله الرحمن الرحيم
r الحمد لله رب العالمين، وصلى الله وسلم على رسوله


በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።
ተከታታይ የእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች) ትምህርት ከኢርሻድ ኪታብ
 ክፍል 5
 የእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረት) ማእዘናት የሚከተሉት ናቸው።
በአላህ ማመን።
በመላኢኮች ማመን።
በመጻህፍት ማመን።
በመልእክተኞች ማመን።
በመጨረሻው ቀን ማመን።
በቀደር ማመን።
  እነዚህ የተጠቀሱት የእስልምና ዓቂዳ ማእዘናት ለመሆናቸው ከቁርአንና ከሓዲስ ብዙ ማስረጃዎች አሉ።

Thursday, June 26, 2014

አዛኙ ጌታ(አላህ) ከዓርሽ በላይ ነው።



- ﺑﺴﻢ اﻟﻠﻪ اﻟﺮﺣﻤﻦ اﻟﺮﺣﻴﻢ -
በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እና አዛኝ በሆነው።



(الرَّحْمَٰنُ عَلَى الْعَرْشِ اسْتَوَىٰ)
[سورة طه : 5]

አዛኙ ጌታ(አላህ) ከዓርሽ በላይ ነው።


Allah is above the throne.


Saturday, June 21, 2014

ኡሱሉ ሰላሳ ኦድዬ ፋይል ክፍል 4


ኡሱሉ ሰላሳ

ኦድዬ ፋይል 

ክፍል 4

3.28 MB ከሚከተለው ሊንክ ዳውንሎድ አድርጉ

Thursday, June 19, 2014

ተከታታይ የእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች) ትምህርት ከኢርሻድ ኪታብ። ክፍል 4



بسم الله الرحمن الرحيم
الحمد لله رب العالمين، وصلى الله وسلم على رسوله


በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።

ተከታታይ የእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች) ትምህርት ከኢርሻድ ኪታብ።  


ክፍል 4

የእስልምና ዓቂዳ ማለት ምን ማለት ነው?

የእስልምና ዓቂዳ ማለት የእስልምና ሃይማኖት መሰረት የሆኑ እምነቶችን እና ተግባሮችን ጠቅሎ የያዘ ነው። የእስልምና ዓቂዳ እስልምናን ከሌሎች ሃይማኖቶች በዋነኝነት የሚለየው ነው። አንድ ሰው ባለው ዓቂዳ መሰረት ሙስሊም(የእስልምናን ዓቂዳ ከያዘ) ወይንም ከሃዲ(የከሃድያንን ዓቂዳ ከያዘ) ይሆናል ።

Tuesday, June 17, 2014

አልከሶ



አልከሶ ለመሄድ ከተሰናዳክ አሊያም ቤተሰቦችክን ገንዘብ ሰጥተክ ወደዚህ ቦታ ለመሸኘት ከተነሳክ ለማንኛውም ቦታው ላይ አላህ ያወገዛቸው ምን ምን ነገራቶች እንደሚከናወኑ ፍንጭ ልስጥክ አድምጠኝ!!


ግጭት ቁ.1 ዘምዘም ውሃ የሚገኘው በመካ ከተማ በተከበረው አላህ ቤት አቅራቢያ እንጂ ስልጤ ክልል አይደለም ፤ በረካም የሚፈለገው ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለም
(( ኑሕ ሆይ ከኛ በሆነ ሰላም ባንተ ላይና አንተም ጋር ባሉት ሕዝቦች (ትውልድ) ላይ በሆኑ በረከቶችም የተጎናጸፍክ ሆነህ ውረድ)) ሁድ #48



ዕርዳታ የሚጠየቀው ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለም
ዘወትር በቀን በትንሹ አስራሰባት ጊዜ ፋቲሃ ላይ የምንለው ለዚህ መልስ ነው
(( አንተን ብቻ እንገዛለን አንተን ብቻ ዕርዳታ እነጠይቃለን)) ፋቲሐህ #5



በረካ የሚሰጠው አላህ እንጂ የቀብር አፈር አይደለም
(( (ኢሳም አለ) በየትም ስፍራ ብኾን ብሩክ አድርጎኛል)) መርየም ‪#‎ሰላሳ‬ አንድ



ጉዳይን የሚያስፈፅመው ችግር እንዲያስወግድልን ዕርዳታ የሚጠየቀው አላህ ብቻ ነው
((ወይም ያ ችግረኛን በለመነው ጊዜ የሚቀበል መከራንም የሚያስወግድ በምድርም ላይ ምትኮች የሚያደርጋችሁ፤ (ይበልጣልን? ወይስ የሚያጋሩት?) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? ጥቂትንም አትገሠጹም። )) አል፡ነምል ስድሳ ሁለት



ወደሳቸው_ቀርቦ_ልክ_ስጁድ_ያህል_በማጎንበስ_እጃቸውን_ለአፍታ_ስሞ_መውጣት
ስለት የሚገባውም ዕርዳታ የሚጠየቀውም ሱጁድ የሚገበደድለትም አላህ ብቻ ነው
«ስግደቴ፣ መገዛቴም፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ነው» በል፡፡ አንዓም#162


(( ረሱል ሰላላሁአለይሂወሰለም « ከከሃዲዎች ጋር የተመሳሰለ ከነርሱ ነው» ))


ዝናብ የሚለመነው አንድ አላህ ብቻ ነው ዕርድም የሚገባው እርሱ ብቻ ነው
(( ስለዚህ ለጌታህ ስገድ፤ (እርድ) ሠዋም (ለርሱ ብቻ) )) ከውሠር #2


ድረስልኝ የምንለው አላህን ብቻ ነው
((ብትጠሩዋቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም፤ ቢሰሙም ኖሮ ለናንተ አይመልሱላችሁም)) ፈጢር #14


(( ረሱል ሰላላሁአለይሂወሰለም «ከአላህ ውጪ ባለ ፍጡር የማለ በርግጥ አጋርቷል»))


(( የዒምራን ባለቤት (ሐና) «ጌታዬ ሆይ፦ እኔ በሆዴ ውስጥ ያለውን (ፅንስ ከሥራ) ነጻ የተደረገ ሲኾን ለአንተ ተሳልኩ፡፡ ከእኔም ተቀበል አንተ ሰሚው ዐዋቂው ነህና»ጊዜ (አስታውስ) )) ዒምራን #35
____


አላህ ቤተሰቦችክን በጀነት እንዲያኖራቸው ከፈለግክ ከዚህ ስፍራ መሄድን እንዲቆጠቡ አሁኑኑ አድርግ (አልረፈደም)
ይሄን መረጃ አልከሶ ቦታው ድረስ በመሄድ ዱዓቶችንና ከዚህ (ከ አልከሶ) በተሰብ ወደ ሱና የተመለሱ ሰዎችን ጠይቆ መረጃ ያቀበለኝን ወንድሜ ኡመር ኢብኑ ኡመር አላህ እጥፍ ድርብ ምንዳ ይሸልምልኝ ::
___________

አላህ ቤተሰቦቻችንን ወደ ተውሂድ ይምራልን ፤ ባለማወቅ የሚያደርጉትንም ሂዳያ ይስጣቸው ፤ ለሽርክና ቢድዓ ጥብቅና የሚቆሙትን አላህ ሂዳያ ይስጣቸው



Saturday, June 14, 2014

ኡሱሉ ሰላሳ ኦድዬ ፋይል ክፍል 3





ኡሱሉ ሰላሳ
ኦድዬ ፋይል 
ክፍል 3
3.56 MB ከሚከተለው ሊንክ ዳውንሎድ አድርጉ

Thursday, June 12, 2014

ተከታታይ የእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች) ትምህርት ከኢርሻድ ኪታብ። ክፍል 3




بسم الله الرحمن الرحيم

الحمد لله رب العالمين، وصلى الله وسلم على رسوله

በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።
ተከታታይ የእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች) ትምህርት ከኢርሻድ ኪታብ።
ክፍል 3


ስለዚህ ባጠቃላይ የእስልምናን ዓቂዳ(የእስልምናን መሰረት)
መማር(ማወቅ)፥ ተግባራዊ ማድረግ፥ ሰዎችን ማስተማር(ጥሪ 
ማድረግ)፥ እነዚህን 3ት ነገሮችን ስንሰራ ለሚደርስብን ችግር ትዕግስት ማድረግ፥ ግዴታ ነው።

Tuesday, June 10, 2014

(New App) የአንድሮይድ አፕሊኬሽን "አሳሳቢ ትምህርቶች ለህዝበ ሙስሊሙ"





"አሳሳቢ ትምህርቶች ለህዝበ ሙስሊሙ" 
(New App) የአንድሮይድ አፕሊኬሽን
― ― ― ― ― ― ― ― ―

ምስጋና ለአለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ነው። የአላህ ሰላምና እዝነት በነብያችን ሙሐመድ ﷺ እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ሁሉ ላይ ይሁን።

በአላህ ፍቃድ በመስከረም 2004 “አሳሳቢ ትምህርቶች ለህዝበ ሙስሊሙ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀዉን የሸይኽ ኢብኑ ባዝ መጽሀፍ ትርጉም ለህትመት ማብቃታችን ይታወሳል። ከመጽሀፉ አስፈላጊነት አንጻር ተደራሽነቱን በማስፋት ብዙ ሰዎች እንዲጠቀሙበት ለማድረግ በሞባይል አፕሊኬሽን App አዘጋጅተን ስናቀርብ ከፍተኛ ደስታ ይሰማናል። 

ትምህርትን እንደ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ካሉ ታላላቅ ኡለማዎች መቅሰም ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ ስለሆነ ትምህርቱን በሚገባ መቅሰምና ለሌሎችም ማስተላለፍ ይጠበቅብናል። ሸይኹ መጽሀፉን በስርዓተ ትምህርት መልክ ከፋፍለው ስላዘጋጁት የቤተሰብ አባላት በእለታዊ ትምህርት መልክ ጊዜ ሰጥተው ቢቀስሙት መሰረታዊ እዉቀትን እንደሚያስጨብጣቸው አያጠራጥርም።
ጸሀፊዉን አላህ ስራቸዉን እንዲቀበላቸው እና ምህረቱን እንዲለግሳቸው እንማጸነዋለን። በትርጉምና በማረም፣ በህትመት እንዲሁም ይህንን App በማዘጋጀት ሂደት አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሁሉ አላህ መልካም ምንዳን እንዲከፍላቸው እንለምነዋለን።

ረጀብ 30/ 1435

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ


Friday, June 6, 2014

ልብን ማጥራትና ስራን ማሳመር





ከአቡ ሑረይራ እንደተዘገበው የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል ‹‹አላህ ወደመልካችሁና ወደ ገንዘቦቻችሁ አይመለከትም ነገር ግን ወደ ልቦቻችሁና ወደ ስራዎቻችሁ ይመለከታል ፡፡ (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል) 


1.ከሰዎች የሚፈለገው ትልቁ ነገር የፀዳ ልብና ያማረ ተግባር ነው፡፡
2.ልብን ማፅዳት ማለት ከሽርክ ፣ ከምቀኝነት ፣ በሰዎች ከመመካት ፣ ሙስሊምን ከመጥላትና ከመሳሰሉት የልብ በሽታዎች መጠበቅ ማለት ሲሆን ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ልብ ካማረ አካል ሙሉ ያምራል ብለዋል፡፡
3.ስራ ተቀባይነት የሚኖረው ለአላህ ብቻ ጥርት ተደርጎ ሲሰራና የነብዩን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) መመሪያ የተከተለ ሲሆን ብቻ ነው፡፡
4.መልካም ስራን ማብዛት አላህ ዘንድ ደረጃን ከፍ ያደርጋል፡፡
5.ሰዎች የሚለኩት በውበትና በገንዘብ ሳይሆን ለአላህ ባላቸው ፍራቻና መልካም ስራ ነው፡፡
6.አላህ ሀብት የሰጠው ሰው ሀብቱን በመልካም ነገር ላይ ካላዋለው አላህ ዘንድ ይጠየቅበታል፡፡
7.ሙስሊም ገንዘብ ስሌለለው መናቅ ወይም ገንዘቡ ብሎ ማክበር የሙስሊም ባህሪ አይደለም




የተወሰደ

Tuesday, June 3, 2014

ኡሱሉ ሰላሳ ኦድዬ ፋይል ክፍል 2




ኡሱሉ ሰላሳ

ኦድዬ ፋይል 

ክፍል 2

3.59 MB ከሚከተለው ሊንክ ዳውንሎድ አድርጉ

Sunday, June 1, 2014

ተከታታይ የእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች) ትምህርት ከኢርሻድ ኪታብ። ክፍል 2



بسم الله الرحمن الرحيم


الحمد لله رب العالمين، وصلى الله وسلم على رسوله



በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።



ተከታታይ የእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች) ትምህርት ከኢርሻድ ኪታብ።



ክፍል 2



የእስልምናን ዓቂዳ ለራሳችን ከተማርን እና ካወቅን ቡሃላ ተግባራዊ ማድረግ አለብን። ተግባራዊ ያልሆነ ማወቅ እወቀት አይባልም። ቀጥሎ የሚመጣው ደረጃ ደግሞ ሰዎችን ወደዚህ ንጹህ እምነት መጥራት ነው። ለራሳችን አውቀናል ወይንም ሰርተናል ብሎ ሰው እየጠመመና እየተሳሳተ ዝም ብሎ ማየት በእስልምና የተወገዘ ተግባር ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን የዚህ እውቀትና ተግባር ባለቤት የሆነውም ዝም በማለቱ እሱ ራሱ ሊጠምም ይችላል።