Tuesday, September 30, 2014

ተከታታይ የእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች) ትምህርት ከኢርሻድ ኪታብ። ክፍል 7


بسم الله الرحمن الرحيم

r الحمد لله رب العالمين، وصلى الله وسلم على رسوله 

በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።
ተከታታይ የእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች) ትምህርት ከኢርሻድ ኪታብ።

ክፍል 7

1.1. ተውሒድ አር-ሩቡብያ

ተውሒር አር-ሩቡብያ ማለት አላህን በስራዎቹ ብቸኛ ማድረግ ነው። አላህን በስራዎቹ ብቸኛ ማድረግ ደግሞ የሚከተሉትን ነጥቦች አውቆ(ተረድቶ) በነሱ ማመንን ያጠቃላል። 
ሁሉንም አለማት የፈጠረው አንድ አላህ ነው።
ሲሳይ ሰጪ አንድ አላህ ነው።
ሂያው አድራጊ፣ ከህያው ነገርም ሙታንን የሚያወጣ አንድ አላህ ብቻ ነው።
ሂደቶች ሁሉ እንዲከሰቱ የሚያደርገው አንድ አላህ ብቻ ነው።