Thursday, May 29, 2014

ተውሂዱል አስማኢ ወሲፋት (አላህ በስሞችና ባህሪያቱ ብቸኛ መሆኑን ማመን)



አንደኛ፡ ትርጉሙ፦

ተውሂዱል አስማኢ ወሲፋት (አላህ በስሞችና ባህሪያቱ ብቸኛ መሆኑን ማመን) ማለት አላህና መልዕክተኛ ያፀደቁትን ስሞችና ባህሪ ማፅደቅና እነሱ ያስወገዱትን ባህሪዎች ደግሞ ከእርሱ ማስወገድ፤ እንዲሁም በትክክለኛው ትርጉሞቻቸውና በሚያሳድሩት አዎንታዊ ተፅዕኖ ማመን ማለት ነው፡፡
ሁለተኛ፡ ስምና ባህሪዎችን ለማፅደቅ ትክክለኛው መንገድ፦
የአላህ ስሞችና ባህሪዎችን ለማፅደቅ ትክክለኛው መንገድ አላህና መልዕክተኛው ያረጋገጡትን ያለ “ተህሪፍ” (ትርጉሙ ሳይዛባ) ፣ ያለ “ተዕጢል” (ትርጉም የለሽ ሳይደረግ)፣ ያለ “ተክይፍ” (አይነቱ ሳይጠቀስ) እና ያለ “ተምሢል” (አምሳል ሳይደረግለት) ማመን ነው፡፡
ተህሪፍ (ትርጉሙን ማዛባት)
ተህሪፍ (ትርጉሙን ማዛባት) የተፈለገውን ትርጉም መቀየር ማለት ሲሆን በሁለት አይነቶች ይከፈላል፦
1. “ተህሪፉ ለፍዝ” (ቃሉን ማጥመም) ይህ የሚሆነው የቁርአን ወይም የሀዲስ ቃላቶች ላይ ሌላ ቃልን በመጨመር፣በመቀነስ ወይም አነባቡን በመለወጥ ነው፡፡ 
ለምሳሌ الرَّحْمَٰنُ عَلَى الْعَرْشِ اسْتَوَىٰ [٢٠:٥] 
ኢስተዋ` የሚለውን `ኢስተውላ` በሚል መቀየር:: (በዚህ ሳቢያ አላህ ዐርሽ ላይ ተደላደለ በሚል የሚሰጠውን ትርጉም ዐርሽን ተቆጣጠረ በሚል እንዲለወጥ ያደርጋል::) 
2. ተህሪፉል መዕና (ትርጉሙን ማጣመም) የቁርአንና የሀዲስን ቃሎች አላህ ባልፈለገው ትርጉም መተርጐም ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ “የድ” (እጅ) የሚለውን ሀይል ወይም ፀጋ በማለት ትርጉሙን መለወጥ:: 
እንዲህ አይነቱ ትርጓሜ ሸሪዓውም ሆነ ቋንቋው አይቀበሉትም፡፡
“ተዕጢል” (ትርጉም የለሽ ማድረግ)
“ተዕጢል” (ትርጉም የለሽ ማድረግ) አላህ በምንም ባህሪ አይገለፅም ብሎ ማስተባበል ማለት ነው፡፡
በ”ተህሪፍ” እና በ”ተዕጢል” መካከል ያለው ለውጥ፡- “ተህሪፍ” ማስረጃዎች የሚደግፉትን ትክክለኛ ትርጉም በሐሰት ትርጉም መቀየር ሲሆን “ተዕጢል” ደግሞ ትክክለኛውን ትርጉም አግልሎ ያለ ተለዋጭ ትርጉም መተው ነው፡፡

“ተክይፍ” የባህሪውን ሁኔታና አይነት መወሰን
“ተክይፍ” የባህሪውን ሁኔታና አይነት መወሰን ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ የአላሀ እጅ እንዲህ አይነት ነው፣ አላህ ዐርሽ ላይ ሲደላደል በእንዲህ አይነት ሁኔታ ነው በመሳሰሉት መልኩ መዘርዘር ማለት ሲሆን ይህ ተግባር ስህተት ነው፡፡ ምክንያቱም ከአላህ በቀር የእርሱን ባህሪ ሁኔታ የሚያውቅ የለም፤ ፍጡራን ይህን ማወቅ አይችሉም፡፡
“ተምሢል” የአላህን ባህሪያቶች ማመሳሰል
“ተምሢል” የአላህን ባህሪያቶች ማመሳሰል ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ የአላህ መስሚያ እንደኛ ነው፣ የእርሱ ፊት እንደኛ ፊት ነው ማለት ነው፡፡
በዚህ ርዕስ ውስጥ ሶስት መሰረቶችን ተግባራዊ ማድረግ በአላህ ስሞችና ባህሪዎች ዙሪያ የተስተካከለ አቋም እንዲኖር ይረዳል፡፡
አንደኛው መሠረት፡ የአላህን ባህሪ ከፍጡራን ጋር ከማመሳሰል መጠንቀቅ፡፡
ሁለተኛው መሠረት፡ አላህና መልዕክተኛው እርሱን በሰየሙበት ስሞችና በገለፁበት ባህሪያት በሚገባው መልኩ ማመን፡፡
ሶስተኛው መሠረት፡ የአላህን ባህሪያት አይነትና ሁኔታዎችን ማወቅ ስለማይቻል ለማወቅ ከመቋመጥ መቆጠብ፡፡
እነዚህን ሶስት መሠረቶች ያረጋገጠ በአላህ ስሞችና ባህሪዎች ትክክለኛ የሆነውንና ታላላቅ ዑለማዎች ያፀደቁትን እምነት ያረጋግጣል፡፡

የተወሰደ።

Tuesday, May 27, 2014

ተከታታይ የእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች) ትምህርት ከኢርሻድ ኪታብ። ክፍል 1



بسم الله الرحمن الرحيم 

الحمد لله رب العالمين، وصلى الله وسلم على رسوله



በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።

ተከታታይ የእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች) ትምህርት ከኢርሻድ ኪታብ።
ክፍል 1
የእስልምናን ዓቂዳ መማር በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። 
የ እስልምናን ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች)  ማወቅ ማለት የሚከተሉትን ነጥቦች አካቶ የያዘ ነው።
1.  የእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች)  ማለት ምን ማለት ነው?
2.  የእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች)  ማእዘናት የትኞቹ ናቸው?
3.  የእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች)ን የሚያፈርሱት(ተቃራኒዎች) ተግባራት እና እምነቶች የትኞቹ ናቸው?
4.  የእስልምና ዓቂዳ(የእስልምና መሰረቶች)ን ጎዶሎ የሚያደርጉት ተግባራት እና እምነቶች የትኞቹ ናቸው?  

Sunday, May 25, 2014

ኡሱሉ ሰላሳ ኦድዬ ፋይል ክፍል 1




ኡሱሉ ሰላሳ

ኦድዬ ፋይል 

ክፍል 1

 ከሚከተለው ሊንክ ዳውንሎድ አድርጉ




Friday, May 23, 2014

‎ተውሂዱል ኡሉሒያ‬

  


“ኡሉሒያ” (አምላክነት) “ኢላህ” (አምላክ) ከሚለው ስም የተወሰደ ሲሆን የሚመለክና ትዕዛዙ ሊፈፀም የሚገባ ማለት ነው፡፡ “ኢላህ” (አምላክ) ከአላህ ውብ ስሞች አንዱ ሲሆን “ኡሉሂያ” (አምላክነት) ደግሞ ከታላቅ ባህሪያቱ አንዱ ነው፡፡
አላህ ልቦች ሊያመልኩት፣ ሊዋረዱለትና ትዕዛዙን ሊፈፅሙ የሚገባ አምላክ ነው፡፡ ምክንያቱም ፍጥረተ ዓለምን የፈጠረ፣ ጉዳዮችን የሚያስተናብር፣ በተሟሉ ባህሪዎች ሁሉ የተገለፀ፣ ከጉድለቶች ሁሉ የተጥራራ ትልቅ ጌታ ነው፡፡
መዋረድና መተናነስ ለርሱ እንጂ ለማንም አይገባም፡፡ በመፍጠር በማስገኘትና እንደነበር በመመለስ ብቸኛና ማንም ማይጋራው ስለሆነ በአምልኮም ማንም ሊጋራው ማይገባ ብቸኛ መሆኑ የግድ ነው፡፡

“ተውሂዱል ኡሉሂያ” አላህን በአምልኮ ብቸኛ ማድረግ ሲሆን ይህም የሚሆነው አንድ ባሪያ በትክክል መመለክ የሚገባው አላህ ብቻ መሆኑን እርግጠኛ ሆኖ ሲያውቅ ነው፡፡ የመመለክ ባህሪ ከአላህ ሌላ ለማንኛውም ፍጡር እንደሌለ ሲያውቅ ውስጣዊና ውጫዊ በሆኑ የአምኮ ዘርፎች በሙሉ አላህን ብቸኛ በማድረግ እንደ ሰላት፣ ዘካ፣ ፆም፣ ሀጅ፣ በመልካም ማዘዝ፣ ከመጥፎ መከልከል፣ ወላጆችን መታዘዝ፣ ዝምድናን መቀጠልና የመሳሰሉትን አካላዊ አምልኮዎችንና እንደ በአላህ ማመን፣ በመላኢኮች፣ በመፅሐፎች፣ በመልዕክተኞች፣ በመጨረሻው ቀንና በቀድር ማመን በመሳሰሉት ልባዊ እምነቶች አላህን ብቸኛ በማድረግ የአላህን ውዴታና የርሱን ምንዳ ብቻ በመከጀል ያመልከዋል፡፡
አላህን በብቸኝነት ማምለክ ግዴታ ስለመሆኑ ብዙና የተለየዩ ማሰረጃዎች አሉ፡-
1. አንዳንዴ በትዕዛዝ መልኩ ይቀርባል::
አላህ እንዲህ ይላል፦
‹‹ ሰዎች ሆይ! የፈጠራችሁን እነዚያንም ከናንተ በፊት የነበሩትን (የፈጠረውን) ጌታችሁን ተገዙ፤ (ቅጣትን) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡ (አል በቀራህ 21)

‹‹አላህንም ተገዙ፡፡ በእርሱም ምንንም አታጋሩ፡፡(አል ኒሳህ 36)
‹‹ጌታህም (እንዲህ ሲል) አዘዘ፡- እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ (ኢስራህ 23)
ይህን የመሳሰሉ አንቀፆች ሌሎችም አሉ፡፡

2. አንዳንዴ ሰዎች ጋኔኖችና ሌሎችም ፍጥረታት የተገኙለት ዋነኛ ዓላማ ተደርጎ ይገለፃል:: አላህ እንዲህ ይላል፦
‹‹ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡ (ዛሪያት 56)

3. አንዳንዴ ይህ የመልክተኞች መላክ አላማ ተደረጐ ይገለፃል፡፡ ለምሳሌ አላህ አንዲህ ይላል-
‹‹በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ «አላህን ተገዙ፤ ጣዖትንም ራቁ» በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፡፡ (ነህል 36)

‹‹ከአንተ በፊትም እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ በማለት ወደርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ (አንቢያ 25)
እነዚህና ሌሎችም ተውሂድን የሚያፀድቁ ወደ እርሱ የሚጣሩ፣ ትሩፋቱን የሚገልፁ፣ የቤተሰቡን ምንዳና የተቃራኒዎችን አደጋ የማያብራሩ የማስረጃ አይነቶች ይጠቀሳሉ፡፡
ኢንሻ አላህ ይቀጥላል...

 


Wednesday, May 21, 2014

ተውሂዱ ሩቡቢያ



ተውሂዱ ሩቡቢያ

ተውሂዱ ሩቡቢያ ማለት፡- አላህ ብቸኛ ፈጣሪ ተቆጣጣሪና ንጉስ መሆኑን ህያው አድራጊ ገዳይ ሲሣይ ለጋሽ እሱ ብቻ እንደሆነና ባጠቃላይ በሚሰራቸው ስራዎች ሁሉ ብቸኛ እንደሆነና አጋር እንደሌለው ማመን ማለት ነው፡፡ 
አላህ እንዲህ ይላል፡- 
‹‹ሰማያትን ያለምታዩዋት አዕማድ (ምሰሶዎች) ፈጠረ፡፡ በምድርም ውስጥ በእናንተ እንዳታረገርግ ተራራዎችን ጣለ፡፡ በእርሷም ላይ ከተንቀሳቃሽ ሁሉ በተነ፡፡ ከሰማይም ውሃን አወረድን፡፡ በእርሷም ውስጥ ከመልካም ዓይነት ሁሉ አበቀልን፡፡ ይህ የአላህ ፍጡር ነው፡፡ እነዚያ ከእርሱ ሌላ ያሉት ምንን እንደፈጠሩ እስኪ አሳዩኝ፡፡ በእውነቱ በዳዮቹ በግልጽ ጥመት ውስጥ ናቸው፡፡ (ሉቅማን 1ዐ-11)

“ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸውን አያችሁን? ከምድር ምንን እንደፈጠሩ አሳዩኝ፤ ወይም በሰማያት ለነሱ (ከአላህ ጋር) መጋራት አላቸውን?” (አል አህቃፍ 4)
ይህ የተውሂድ ክፍል ከእምነት ክፍል ውስጥ አንዱ ቢሆንም አንድ ሰው ይህንን ብቻ በማመኑ በአላህ አመነ አይባልም እንዲያውም በነብዩ ላይ ጦርነት የከፈቱ አጋሪዎች በዚህኛው የተውሂድ ክፍል ያምኑ እንደነበር አላህ በብዙ የቁርዓን አንቀፆች ገልጿል፡፡ 
አላህ እንዲህ ይላል፡-

‹‹ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ፀሐይንና ጨረቃንም የገራ ማን እንደኾነ ብትጠይቃቸው በእርግጥ አላህ ነው ይሉሃል፡፡ ታድያ እንዴት ይመለሳሉ፡፡ (አንከቡት 61)
‹‹ከሰማይም ውሃን ያወረደና በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው ያደረጋት ማን እንደኾነ ብትጠይቃቸው «አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ምስጋና ለአላህ ነው» በላቸው፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡ (አንከቡት 63)
‹‹ማን እንደፈጠራቸውም ብትጠይቃቸው «በእርግጥ አላህ ነው» ይላሉ፡፡ ታዲያ (ከእምነት) ወዴት ይዞራሉ፡፡ (ዙኽሩፍ 87)
«ምድርና በውስጥዋ ያለው ሁሉ የማን ነው? የምታውቁ ብትኾኑ (ንገሩኝ)» በላቸው፡፡ በእርግጥ ‹‹የአላህ ነው» ይሉሃል፡፡ታዲያ አትገሰጹም ፡፡ የሰባቱ ሰማያት ጌታና የታላቁ ዐርሽ ጌታ ማን ነው? «በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ እንግዲያ አትፈሩትምን፡፡ የነገሩ ሁሉ ግዛት በእጁ የኾነ እርሱ የሚጠብቅ በእርሱ ላይ የማይጠበቅ ማን ነው? የምታውቁ እንደኾናችሁ (መልሱልኝ)» በላቸው፡፡ በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ እንዴት ትታለላላችሁ?» በላቸው፡፡ (አል ሙእሚኑን 84-89)
ከዚህ የምንረዳው በተውሂዱ ሩቡቢያህ ማመን ብቻ አንድን ሰው ከቅጣት እንደማያድነው እና ሙስሊምም እንደማያሰኘው ነው፡፡ ስለዚህ በአላህ አማኝ ሙስሊም ለመሆን አምልኮን ለአላህ ብቻ በማድረግ በአምልኮው ላይ ከማጋራት መጠንቀቅ ግዴታ ነው::
‪#‎አላማችን‬ መሰረታዊ የሆነውን የተውሂድ እውቀት ለሙስሊሙ ማህብረተሰብ በሰፊው ማድረስ ነው::



Tuesday, May 20, 2014

የሽርክ መገለጫዎች


ርዕስ ፡- የሽርክ መገለጫዎች 

አዘጋጅ፡- ጀማል ያሲን ራጁ
አጭር ማብራሪያ፡- ስለ አስከፊው ሽርክ ምንነት የሚያብራራ ምርጥ ሙሃድራ ::
إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَاءُ ۚ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدِ افْتَرَىٰ إِثْمًا عَظِيمًا [٤:٤٨] 
አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም፡፡ ከዚህ ሌላ ያለውንም (ኀጢአት) ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው ታላቅን ኀጢአት በእርግጥ ቀጠፈ፡፡ (4:48)

ሁላችንም ልናደምጠው የሚገባ አንገብጋቢ ትምህርት!!!!!!!!!!
ዳውንሎድ በማድረግ ያድምጡ ለወዳጅ ዘመድዎም ያስተላልፉ። 
በአላህ ፍቃድ በቀጣይም ጠቃሚ የሆኑ ሙሀደራዎች እንዲሁም መጽሀፍትን የምለቅ ይሆናል ኢንሻ አላህ። 
ከነዚህ አማራጮች አንዱን በመጫን ዳውንሎድ ያድርጉ፡-

Sunday, May 18, 2014

‪ከ አላህ ውጪ እርድ ለማን አይገባው‬!!!


እንደ ቀልድ አንዲት በግ ገዝተህ ማረድህን አትይ ወዳጄ፥ ዝንብ አፍኖ ገድሎ ጀሀነም የተላከ አለና:: እንዲህ ነው ታሪኩ:-
"ሁለት ሰዎች በጣዖት አምላኪዎች ግዛት ያልፉና ሳትገብሩ አትንቀሳቀሱም ይባላሉ:: አንደኛው ግለሰብ እኔ ዘንድ ምንም ነገር የለም ይላቸዋል:: የዚህን ግዜ እንዳው ዝንብ እንኳ ብትሆን ይሉታል:: ሰውዬውም ምን አነታረከኝ ብሎ እፍን ያደርግና ያቀርብላቸዋል፥ መንገድ ተለቀቀለት ማለት ነው - እወቅ! የተለቀቀለት የጀሀነም መንገድ ነው:: 
ሌላኛው ግን በአንጻሩ ከአላህ ውጭ ምንንም ለማንም አካል አልገብርም ቢላቸው አንገቱን ብለው ጀነት ሰደዱት" አሉ መልእክተኛው (ሠለላሁ ዐለይሂ ወሰለም):: 
አላህ ከእኛ እርድ ዱለቱ ወይ ጥብሱ አይሄድለትም አትድከም፣ ስጋው ቆዳው ቀንዱ ደሙ ፈርሱ እዚሁ አንተ ቤት ቀሪ ነው፥ ባይሆን ይህችን አያህ አንብብልኝ:-

لَن يَنَالَ اللَّهَ لُحُومُهَا وَلَا دِمَاؤُهَا وَلَٰكِن يَنَالُهُ التَّقْوَىٰ مِنكُمْ ۚ كَذَٰلِكَ سَخَّرَهَا لَكُمْ لِتُكَبِّرُوا اللَّهَ عَلَىٰ مَا هَدَاكُمْ ۗ وَبَشِّرِ الْمُحْسِنِينَ [٢٢:٣٧
"አላህን ሥጋዎቿም ደሞቿም ፈጽሞ አይደርሰውም፡፡ ግን ከእናንተ የሆነው ፍራቻ ይደርሰዋል፡፡" (22:37)
እንዴታ! አለሞቼ እራቶቼ አለቆቼ ቁጥቦቹ ታረቁን ባክኾን፥ ይኸው ተቀበሉን ..... ጀባ ብለናል ተብሎ ከታረደ ስጋ ለአላህ የሚደርሰው ክፍሉ የቱ ነው እስቲ ልጠይቅህ? ይሄ ይገርምሀል እንዴ? ትንሽ ቆይቶ እኮ ደግሞ አራጁ በሰላቱ ውስጥ እንዲህ ይል ይሆናል: 
"﴿إِنَّآ أَعْطَيْنَـكَ الْكَوْثَرَ - فَصَلِّ لِرَبِّكَ وَانْحَرْ " 
"ስለዚህ ለጌታህ ስገድ፤ (በስሙ) ሰዋም"::
ልብ ያለው ልብ ይበል!!!

 
 ከ     https://www.facebook.com/firsttewhed  የተወሰደ።

Saturday, May 17, 2014

እርዝ



እርዝ



ሀ. ትርጉሙ፦
እርዝ ከክፋት ይጠብቅ ዘንድ ታሽጎ አንገት ላይ የሚንጠለጠል ፅሁፍ፣ ክሮች፣ አጥንቶች የመሳሰሉ ነገሮች ሲሆን ድሮ ዓረቦች በተሳሳተ አመለካከታቸው ልጆችን ከሰው አይን ለመከላከል የሚያንጠለጥሉላቸው ጥቅምን ለማግኘት ወይም ጉዳትን ለመከላከል በማሰብ የሚደረግ ነው፡፡

ለ. ሸሪዓዊ ብይኑ፦
ሀራም (የተከለከለ) ከመሆኑም በላይ ከሽርክ አይነቶች አንዱ ነው፡፡ ምክንያቱ ከአላህ ውጭ በሆነ ነገር መንጠልጠል ነው፡፡
ክፉን መካች አላህ ብቻ በመሆኑ ማንኛውም ሰው ጎጂን ነገር መከላከል ያለበት በአላህ በስሞቹና በባህሪያቱ ብቻ ነው፡፡
ኢብኑ መስዑድ እንዳሉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው ‹‹ሩቃ፣ እርዝና መስተፋቅር መስራት ሽርክ ነው”

አብደላህ ኢብኑ ዑከይም እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል “በአንድ ነገር ላይ የተንጠለጠለ ወደ ለርሱ ይተዋል”
ዑቅበት ኢብን ዓሚር እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል “እርዝን ያንጠለጠለ አላህ አይሙላለት፣ ዛጎልንም ያንጠለጠለ አላህ አይተውለት”
ዑቅበት ኢብን ዓሚር እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል “እርዝን ያንጠለጠለ ሽርክን ፈፅሟል”

እነዚህና መሰል ጥቅሶች ዓረቦች በብዛት ሲያንጠለጥሉት የነበሩትን ሽርካዊ እርዞች የሚከለክሉ ሲሆኑ የተከለከሉትም ከአላህ ውጭ በሆነ ፍጡር ላይ መንጠልጠል በመሆኑ ነው፡፡

ሐ. የሚንጠላጠለው ፅሑፍ የቁርአን ቃል ከሆነ፦
ዑለማዎች በዚህ ዙሪያ አልተስማሙም ከፊሉ የሚፈቅድ ሲሆን ሌላው ደግሞ ይከለክላል፡፡ ቁርአንን ለፈውስ ማንጠልጠል አይቻልም የሚሉ አቋሟቸው ከአራት ምክንያቶች አንፃር ሲታይ ትክክል ነው፡፡

1. ነብዩ እርዝን የከለከሉት በጥቅሉ ሲሆን ይህን አይነቱን ነጥሎ የሚያወጣ ማስረጃ አለመኖሩ፡፡
2. ይህን መፍቀድ ከቁርአን ያልሆነን ፅሁፍ ለማንጠልጠል መንገድ ስለሚከፍትና ወደ መጥፎ የሚመራን መንገድ መዝጋት ደግሞ ተፈላጊ ስለሆነ::
3. አንጠልጣዩ በመፀዳጃ፣ በኢስቲንጃና በመሳሰሉት ቦታ ይዞት ስለሚገኝ ቁርአንን ዝቅ የሚያደርግ በመሆኑ፡፡
4. በቁርአን መፈወስ በምን መልኩ መሆን እንዳለበት ስለተገለፀ (እሱም ህመምተኛው ላይ መቅራት ነው) እና ይህን መተላለፍ ስለማይቻል፡፡

ከ 
www.facebook.com/emnetihintebiq የተወሰደ።

Friday, May 16, 2014

ርዕስ ፡- ዒባዳ


ርዕስ ፡- ዒባዳ

አዘጋጅ፡- ሸይኽ ሙሀመድ ወሌ (ረሂመሁላህ )
አጭር ማብራሪያ፡- ስለ ዒባዳ ምንነት የሚያብራራ ምርጥሙሀደራ::
ዒባዳ ማለት :- አላህ ለሚወዳቸው ውስጣዊም ሆነ ውጫዊ ንግግሮች እና ተግባሮች ሁሉ የተሰጠ ስያሜ
ነው፡፡
ሁላችንም ልናደምጠው የሚገባ አንገብጋቢ ትምህርት!!!!!!!!!!


ዳውንሎድ በማድረግ ያድምጡ ለወዳጅ ዘመድዎም ያስተላልፉ።
በአላህ ፍቃድ በቀጣይም ጠቃሚ የሆኑ ሙሀደራዎች እንዲሁም መጽሀፍትን የምለቅ ይሆናል ኢንሻ አላህ።
ከነዚህ አማራጮች አንዱን በመጫን ዳውንሎድ ያድርጉ፡-


http://goo.gl/nvnAc2
http://goo.gl/Vesw7W
http://goo.gl/DSbJqm

Thursday, May 15, 2014

ነብዩ ﷺ የት ነው ያሉት???

ነብዩ የት ነው ያሉት???

ክፍል 19

‹‹ነበው ዲጅዋ ዲጁ ነብዮ ዲጅዌ›› ‹‹አርሂቡ ነቢ አርሂቡ ነቢ›› ‹‹ግቡልን የተንቢ›› ‹‹መርሃባ ነቢ መርሃባ››
አገራችን ላይ የሚባሉ መንዙማዎች ውስጥ የሚከተሉት ይባላሉ 
‹‹
ነበው ዲጅዋ ዲጁ ነብዮ ዲጅዌ›› 
‹‹
አርሂቡ ነቢ አርሂቡ ነቢ›› 
‹‹
ግቡልን የተንቢ›› 
‹‹
መርሃባ ነቢ መርሃባ››
አስገራሚ ነው፡፡ የአቂዳ ወይንም የእምነት ትምህርት ማህበረሰባችን በሰፊው ሊደርሰው እንደሚገባ የሚጠቁሙ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ የዛሬውም ትምህርት ይህንን ያስይዛል፡፡
ዝምታ መፍትሄ አይሆንም፡፡ ማህበረሰቡን የህይወቱ ማማር በዚህኛውም አለም ይሁን በሚቀጥለው የሚስተካከልበትን ‹‹ተውሂድ›› በሰፊው ማድረስ ግዴታ ነው፡፡
የዛሬው አርስት እንደሚያሳየው ከላይ የተባሉትን አባባሎች እያንዳንዳቸውን እንይ እና ኢስላም የሚለውንም አይተን ከዛ ሃቁን ተቀብለን እንሂድ፡፡ ለአላህ ብሎ መመካከር ኢስላም ያስቀመጠው ግዴታ ነው፡፡
‹‹ነበው ዲጅዋ ዲጁ ነብዮ ዲጅዌ›› የሚለው አባባል ‹‹ሀደሬኛ›› ሲሆን ሃደሬኛ መንዙማ ከሚሉት ሰዎች ውስጥ አንዱ ያለው መንዙማ ነው፡፡ እራሱ ሲተረጉመው እንዲህ ይላል ‹‹ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መጡ መጡ ለማለት ነው›› ብሎ ተረጎመው፡፡ ይህ ሰው ከእርሱ በፊት ለነበረው መንዙማ ባይን አስመልክቶ እንዲህ አለ ‹‹እንዲህ ነብያችንን እያመጧቸው ሸይኽ ሙሃመድ አወል እንደው ስማቸው እየተጠራ ሳለ ቁጭ ማለታችሁ ያሳዝናል፡፡ ስለዚህ ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እሳቸውን ስናወድስ ‹‹ነበው ዲጅዋ ዲጁ ነብዮ ዲጅዌ›› ‹‹ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መጡ መጡ ለማለት ነው›› ›› ብሎ ተረጎመው፡፡
ከዛም ድቤ የሚደበድበው ሰው ተመልካች የነበሩ ሰዎችን ‹‹ተነሱ ብሎ በእጁ ምልክት ሰጣቸው›› እንዲነሱ፡፡
በጉራግኛ ደግሞ ረመዳን ላይ ከወጣ መንዙማ ውስጥ እንዲህ ይላል ‹‹ግቡልን የተንቢ›› ነብያችንን እንደማለት ነው፡፡
ሌላው ደግሞ ‹‹አርሂቡ ነቢ አርሂቡ ነቢ›› እየተባለ ነብያችንን ይመጣሉ ብሎ መገመት እና ማመን ነው፡፡ ይህ ደግሞ በሚቀጥለው ስንኛቸው በደንብ ይብራራል፡፡
‹‹መርሃባ ነቢ መርሃባ›› ሲባል ይህንን ሲሉ እነዚሁ ሰዎች ከተቀመጡበት ይቆማሉ፡፡ አንዳንድ ሰዎች እንዲያውም መንገድ ከመሳታቸው ውስጥ ነጭ ምንጣፍ አስቀምጠው ‹‹ነብያችን እና ሰሃባዎች መጥተው እዚህ ይቀመጣሉ›› ይላሉ፡፡
ኢስላም የሚሰጠውን መልሶች በአላህ ፈቃድ እንደሚከተሉት እንይ
1) የአላህ መላክተኛን እንዲህ ይላቸዋል ‹‹አንተም ሟች ነህ፤ እነሱም ሟቾች ናቸው››፡፡
2) የአላህ መላክተኛ በህይወት በነበሩበት ግዜ ሰሃባዎችን እንዳይቆሙላቸው ከልክለዋል፡፡ ሰሃባዎችም ከእኛ በላይ የአላህ መላክተኛን በጣም የሚያከብሩት ነብያችን አደለም ሞተው በህይወት እያሉም አይቆሙላቸውም ነበር፡፡ ታድያ እነዚህ መንዙማ ባዬች ከሰሃባዎች በላይ ለነብያችን ክብር ኖሯቸው ነውን??? ወደ ቀጥተኛው መንገድ አላህ ይምራን
3) እኛ እሳቸው ላይ ሰለዋት ስናወርድ ምን ብለን ነው???
‹‹
አላህ ሆይ! በሙሃመድ ላይ ሰላትህ እና እዝነትህ ይሁን››፡፡ እንዳየነው ተለማኙ አላህ ነው፡፡ ከአዛን በኋላ የምናደርገው ዱዓ እራሱ የአላህ መላክተኛ እንዲህ ብላችሁ አላህን ለምኑልኝ ነበር ያሉት ‹‹….. ለሙሃመድ ወሲላ እና ፈዲላን (ጀነት ውስጥ ያሉ ደረጃዎች ናቸው ተብሏል) ስጣቸው››፡፡ አማኞች ለአላህ መላክተኛ ነው እየለመኑላቸው ያሉት፤ በህይወት ያለ ለሞቱት ዱዐ ያደርጋል፡፡
4) እኛ እሳቸው ላይ ሰለዋት ስናወርድ እሳቸው በቀጥታ ያውቃሉን ??? ሃዲሱ እንዲህ ይላል
‹‹
የትም ሆናችሁ ሰላም (ሰለዋት ብታወርዱብኝ) ብትሉኝ፤ መላኢካዎች ያደርሱልኛል›› ሃዲሱ እንደሚያሳየው በግልፅ እሳቸው ላይ ሰለዋት ስናወርድ መላኢካዎች ያደርሱላቸዋል፤ እንጂ እመጣለሁ አላሉም፡፡
5) የአላህ መላክተኛ አደለም ሞተው በህይወት በነበሩ ግዜ የአላህን ሀቅ አንዱንም ቢሆን ለእርሳቸው አይገባቸውም፡፡ የአላህ መላክተኛ
- የሩቁን አያውቁም፤
-
ጥሩን ለራሳቸው ማምጣት አይችሉም፤
-
መጥፎን መከላከል አይችሉም አላህ ከጠቀማቸው ውጭ፤
-
አላህ እሳቸውን በጉዳት ቢፈልጋቸው ፍጡራን ተሰብስበው ሊያስጥሏቸው አይችሉም፤
-
መስጠትም፤ መንሳትም አይችሉም፤
-
ታላቁንም ምልጃ አላህን ተደፍተው (ሱጁድ አድርገው) ለምነው አላህ ከፈቀደላቸው በኋላ ብቻ ነው - የሚያማልዱት፤ የሚያማልዱትም አላህ ለፈቀደለት ብቻ ነው፡፡ 
-
ስለዚህ የአላህ መልክተኛ አካላቸው መዲና ተቀብሮ ነው ያለው ሰለዋት ስናወርድባቸው እንኳን ያሉበት ሆነው ነው፤ አላህ ሩሃቸውን መልሶላቸው መልስ የሚሰጡት፡፡ ከዛ ውጭ ‹‹መርሃባ፤ መጡ፤ ግቡልን፤ ዲጅዋእና የመሳሰሉትን›› ማለት ከባድ ስህተት ነው፡፡
ወደ ሰለፉነ ሷሊሁን እምነት፤ ንግግር እና ተግባር አላህ ይመልሰን፡፡ አዲስ መጤ ከተባሉ ነገሮች አላህ ይጠብቀን፡፡ አላህ እውነተኛ አንድነት ይስጠን፡፡

የአላህ ሰላት እና ሰላም በመልክተኞች ሁሉ ላይ ይሁን፡፡