ተውሂድ...የሁሉም ነብያት ተልዕኮ
አላህ በተለየዩ ዘመናት በርካታ ነቢያትን ልኳል፡፡ እነዚህ ነብያት ለተላኩላቸው ሕዝቦች ያስተምሩ የነበረው የአላህን ብቸኛ አምላክነት የሚገልፀውን የተውሂድ ክፍል እንደነበረ ቁርአን ይነግረናል፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፤
{وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِي كُلِّ أُمَّةٍ رَسُولًا أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَاجْتَنِبُوا الطَّاغُوتَ} النحل: ٣٦
‹‹በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ ‘አላህን ብቻ አምልኩ፤ ጣዖትንም ራቁ’ በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፡፡››
አል ነህል 36
በሱረቱል አንቢያእ ውስጥም አላህ ወደየህዝቦቻቸው ስለላካቸው መልዕክተኞች ለነቢያችን ሲገልፅላቸው እንዲህ ይላል፡-
وَمَا أَرْسَلْنَا مِنْ قَبْلِكَ مِنْ رَسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُون
الأنبياء: ٢٥
‹‹ከአንተ በፊትም፤ ‘እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና በብቸኝነት አምልኩኝ’ በማለት ወደርሱ መልእክትን የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡›› አል አንቢያ 25
በየዘመናቱ ወደ ሕዝቦቻቸው የተላኩ ነቢያት ሕዝባቸውን ያስተምሩና ይመክሩ፣ ያስጠነቅቁና ይዘክሩ የነበረው፤ በእምነት ዙሪያ ጠንከር ያለና የፀና አቋም እንዲኖራቸው ነበር፡፡ የአላህ ወዳጆች ጥሪዉን በመቀበል ከባዕድ አምልኮ ሲቆጠቡ፤ ብዙዎች ግን አምላካቸው ለእርሱ የዋለውን ውለታ አመስግነው የእዝነት መልዕክተኞችን መቀበል ሲገባቸው አስተባበሉ፡፡
በሁሉም የአምልኮ ዘርፎች አላህን በብቸኝነት ማምለክ በየዘመናቱ የተላኩ ነቢያት ሁሉ ጥሪ ነበር፡፡ በተለይ በእምነት ዙሪያ ያሉ የዲን ጉዳዮችን ችላ ማለት ለጥፋት ያበቃል፡፡ የአላህን ውዴታና እርዳታ የምናገኘው ይህንን የነብያት ጥሪ ተቀዳሚ አጀንዳ አድርገን ትኩረት ስንሰጠው ነው።
አላህ ለተውሂድ ኖረን በተውሂድ የምንሞት ያድርገን!
አሚን
ዓላማችን ኢስላማዊ እውቀትን ማዳረስ ነው::

No comments:
Post a Comment