"አሳሳቢ ትምህርቶች ለህዝበ ሙስሊሙ"
(New App) የአንድሮይድ አፕሊኬሽን
― ― ― ― ― ― ― ― ―
ምስጋና ለአለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ነው። የአላህ ሰላምና እዝነት በነብያችን ሙሐመድ ﷺ እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ሁሉ ላይ ይሁን።
በአላህ ፍቃድ በመስከረም 2004 “አሳሳቢ ትምህርቶች ለህዝበ ሙስሊሙ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀዉን የሸይኽ ኢብኑ ባዝ መጽሀፍ ትርጉም ለህትመት ማብቃታችን ይታወሳል። ከመጽሀፉ አስፈላጊነት አንጻር ተደራሽነቱን በማስፋት ብዙ ሰዎች እንዲጠቀሙበት ለማድረግ በሞባይል አፕሊኬሽን App አዘጋጅተን ስናቀርብ ከፍተኛ ደስታ ይሰማናል።
ትምህርትን እንደ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ካሉ ታላላቅ ኡለማዎች መቅሰም ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ ስለሆነ ትምህርቱን በሚገባ መቅሰምና ለሌሎችም ማስተላለፍ ይጠበቅብናል። ሸይኹ መጽሀፉን በስርዓተ ትምህርት መልክ ከፋፍለው ስላዘጋጁት የቤተሰብ አባላት በእለታዊ ትምህርት መልክ ጊዜ ሰጥተው ቢቀስሙት መሰረታዊ እዉቀትን እንደሚያስጨብጣቸው አያጠራጥርም።
ጸሀፊዉን አላህ ስራቸዉን እንዲቀበላቸው እና ምህረቱን እንዲለግሳቸው እንማጸነዋለን። በትርጉምና በማረም፣ በህትመት እንዲሁም ይህንን App በማዘጋጀት ሂደት አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሁሉ አላህ መልካም ምንዳን እንዲከፍላቸው እንለምነዋለን።
ረጀብ 30/ 1435
ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

No comments:
Post a Comment