Tuesday, June 17, 2014

አልከሶ



አልከሶ ለመሄድ ከተሰናዳክ አሊያም ቤተሰቦችክን ገንዘብ ሰጥተክ ወደዚህ ቦታ ለመሸኘት ከተነሳክ ለማንኛውም ቦታው ላይ አላህ ያወገዛቸው ምን ምን ነገራቶች እንደሚከናወኑ ፍንጭ ልስጥክ አድምጠኝ!!


ግጭት ቁ.1 ዘምዘም ውሃ የሚገኘው በመካ ከተማ በተከበረው አላህ ቤት አቅራቢያ እንጂ ስልጤ ክልል አይደለም ፤ በረካም የሚፈለገው ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለም
(( ኑሕ ሆይ ከኛ በሆነ ሰላም ባንተ ላይና አንተም ጋር ባሉት ሕዝቦች (ትውልድ) ላይ በሆኑ በረከቶችም የተጎናጸፍክ ሆነህ ውረድ)) ሁድ #48



ዕርዳታ የሚጠየቀው ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለም
ዘወትር በቀን በትንሹ አስራሰባት ጊዜ ፋቲሃ ላይ የምንለው ለዚህ መልስ ነው
(( አንተን ብቻ እንገዛለን አንተን ብቻ ዕርዳታ እነጠይቃለን)) ፋቲሐህ #5



በረካ የሚሰጠው አላህ እንጂ የቀብር አፈር አይደለም
(( (ኢሳም አለ) በየትም ስፍራ ብኾን ብሩክ አድርጎኛል)) መርየም ‪#‎ሰላሳ‬ አንድ



ጉዳይን የሚያስፈፅመው ችግር እንዲያስወግድልን ዕርዳታ የሚጠየቀው አላህ ብቻ ነው
((ወይም ያ ችግረኛን በለመነው ጊዜ የሚቀበል መከራንም የሚያስወግድ በምድርም ላይ ምትኮች የሚያደርጋችሁ፤ (ይበልጣልን? ወይስ የሚያጋሩት?) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? ጥቂትንም አትገሠጹም። )) አል፡ነምል ስድሳ ሁለት



ወደሳቸው_ቀርቦ_ልክ_ስጁድ_ያህል_በማጎንበስ_እጃቸውን_ለአፍታ_ስሞ_መውጣት
ስለት የሚገባውም ዕርዳታ የሚጠየቀውም ሱጁድ የሚገበደድለትም አላህ ብቻ ነው
«ስግደቴ፣ መገዛቴም፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ነው» በል፡፡ አንዓም#162


(( ረሱል ሰላላሁአለይሂወሰለም « ከከሃዲዎች ጋር የተመሳሰለ ከነርሱ ነው» ))


ዝናብ የሚለመነው አንድ አላህ ብቻ ነው ዕርድም የሚገባው እርሱ ብቻ ነው
(( ስለዚህ ለጌታህ ስገድ፤ (እርድ) ሠዋም (ለርሱ ብቻ) )) ከውሠር #2


ድረስልኝ የምንለው አላህን ብቻ ነው
((ብትጠሩዋቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም፤ ቢሰሙም ኖሮ ለናንተ አይመልሱላችሁም)) ፈጢር #14


(( ረሱል ሰላላሁአለይሂወሰለም «ከአላህ ውጪ ባለ ፍጡር የማለ በርግጥ አጋርቷል»))


(( የዒምራን ባለቤት (ሐና) «ጌታዬ ሆይ፦ እኔ በሆዴ ውስጥ ያለውን (ፅንስ ከሥራ) ነጻ የተደረገ ሲኾን ለአንተ ተሳልኩ፡፡ ከእኔም ተቀበል አንተ ሰሚው ዐዋቂው ነህና»ጊዜ (አስታውስ) )) ዒምራን #35
____


አላህ ቤተሰቦችክን በጀነት እንዲያኖራቸው ከፈለግክ ከዚህ ስፍራ መሄድን እንዲቆጠቡ አሁኑኑ አድርግ (አልረፈደም)
ይሄን መረጃ አልከሶ ቦታው ድረስ በመሄድ ዱዓቶችንና ከዚህ (ከ አልከሶ) በተሰብ ወደ ሱና የተመለሱ ሰዎችን ጠይቆ መረጃ ያቀበለኝን ወንድሜ ኡመር ኢብኑ ኡመር አላህ እጥፍ ድርብ ምንዳ ይሸልምልኝ ::
___________

አላህ ቤተሰቦቻችንን ወደ ተውሂድ ይምራልን ፤ ባለማወቅ የሚያደርጉትንም ሂዳያ ይስጣቸው ፤ ለሽርክና ቢድዓ ጥብቅና የሚቆሙትን አላህ ሂዳያ ይስጣቸው



No comments:

Post a Comment