Tuesday, November 25, 2014

የመውሊድ በዓል በቁርዓንና በሐዲስ መሠረት አለው ብሎ መድከም ከንቱ መሆኑን ማወቅ ይገባል፡፡



የመውሊድ በዓል በቁርዓንና በሐዲስ መሠረት አለው ብሎ መድከም ከንቱ መሆኑን ማወቅ ይገባል፡፡ መውሊድ በነቢዩ የሕይወት ዘመን ፈፅሞ እንዳልነበረ ዑላማዎች ሁሉ ይስማሙበታል፡፡ እንዲያውም መውሊድን የሚያከብሩት ሳይቀሩ ይህንን እውነታ አያስተባብሎም፡፡

ይህ አይነቱ የመልእክተኛዉ ፈለግ የሌለበት ተግባር ደግሞ ወደ አላህ መቃረቢያ መንገድ መሆን እንደማይችል በበርካታ ቁርአናዊና ሀዲሳዊ አስረጆች ተብራርቷል፡፡

በዓሉ መከበር የጀመረዉ ከአራተኛዉ የሒጅራ ክፍለ ዘመን በኋላ ራሳቸዉን “ፋጢሚዬች” ብለው ይጠሩ በነበሩ የኡበይድ አልቀዳህ ዘሮች ነው በግብፅ ነው፡፡


መዉሊድ እንደማይፈቀድ ለማስረዳት ከዚህ የተሻለ ግልጽ አስረጅ የለም። መልካም ተግባር ቢሆን የነብዩ ባልደረቦች ቀድመዉን በተገበሩት ነበር። የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል

‹‹በዚህ በጉዳያችን (በዲናችን) ከእርሱ ያልሆነን ነገር የፈጠረ (ስራው) ተመላሽ ነው፡፡›› አል ቡኻሪይ 2550 እንዲሁም ሙስሊም በቁጥር 1718 ከአዒሻ ዘግበውታል

 ye haji welea sle mewlid daewa lemadamet yihinin link yichanu 





No comments:

Post a Comment